በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ የአጎአ ተጠቃሚነት የወደፊት ሁኔታ


የኢትዮጵያ የአጎአ ተጠቃሚነት የወደፊት ሁኔታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:16 0:00

የኢትዮጵያ የአጎአ ተጠቃሚነት የወደፊት ሁኔታ

ኢትዮጵያ ከአጎአ እድል ተጠቃሚነት የምትታገድ ከሆነ እስከ 200 ሺህ ሰራተኞች የስራ ዕድል ሊያጡ እንደሚችሉ ተጠቆመ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይን መነሸ በማድረግ ኢትዮጵያ የተለያዩ ምርቶችን ከቀረጥ ነጻ ለዩናይትድ ስቴትስ ገበያ የማቅረብ ተጠቃሚነቷ ቢነሳ፣ ምስኪን ሴቶች የተፈጠረላቸውን የስራ ዕድልን በማሳጣት ሌላ የሰብዓዊ መብት ጥያቄ እንደሚያስከትል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰንዶካን ደበበ ለቪኦኤ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአጎአ እድል ተጠቃሚነት የመቀጠል እና ያለመቀጠሏ ጉዳይ በቅርቡ እንደሚወሰን የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የንግድ ተወካይ የሆኑት ካትሪን ታይ፣ በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ኢሰመኮ በትግራይ ክልለ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የተመለከተ ሪፖርት ከ3 ቀናት በኋላ የሚያቀርቡ ሲሆን ይህን ተከትሎ አዳዲስ ውሳኔዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም ይጠበቃል፡፡

XS
SM
MD
LG