በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዕድገት ዕድል ድንጋጌ (አጎአ)አባል ሆና መቀጠል ይናርባታልን?


በሐዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ ከሚገኙ ፋብሪካዎች መካከል በአንዱ የሚገኙ ሰራተኞች በስራ ላይ (ህዳር 2010)
በሐዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ ከሚገኙ ፋብሪካዎች መካከል በአንዱ የሚገኙ ሰራተኞች በስራ ላይ (ህዳር 2010)

በጎረጎሳዊያኑ 2000 ዓመተምህረት የተፈረመው የአፍሪካ ዕድገት ዕድል ድንጋጌ (አጎአ) ዩናትይድ ስቴትስ እና አፍሪካዊያን ሀገራትን በንግድ ዘርፍ ያጣመረ ሰነድ ነው። ኢትዮጵያ ከዚህ ድንጋጌ ተጠቃሚዎች መካከል አንዷ ስትሆን ፣ በእየዓመቱ በመቶ ሚሊየኖች ዶላር የሚያወጣ ሸቀጥ ወደ አሜሪካ ምድር ያለ ቀረጥ እንድትልክም አስችሏታል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ጦርነት ውስጥ ትገኛለች ።በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የተቀሰቀሰው አንድ ዓመት ያስቆጠረው ጦርነት ፤ እሱን የተከተሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክሶች ሀገሪቱ ከዓለም አቀፍ ተቋማት እና ዩናይትድ ስቴትስን ከመሰሉ አጋር አገራት ጋር በነበራት ግንኙነት ላይ ፈተና ደቅኗል።የሀገራትን ሰብዓዊ መብት ይዞታ እንደ አንድ መስፈርት ከሚቆጥረው አጎአ አባልነት ልትሰረዝ እንደምትችል ስጋት አይሏል።

ይሁንና ይሄ እንዳይሆን ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሰሞነኛ እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ሀብታሙ ስዩም በሰሜን አሜሪካ መሰሉን ዘመቻ የሚያስተባብሩ ግለሰቦችን አነጋግሯል ። አብሮም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁለንተናዊ ችግር ለመቅረፍ ካስፈለገ ስረዛን የመሰሉ ጫና መፍጠሪያ እርምጃዎች መኖራቸውን የሚደግፉ ግለሰብ ሀሳብም በቀጣዩ ውይይት ተካቷል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዕድገት ዕድል ድንጋጌ (አጎአ)አባል ሆና መቀጠል ይኖርባታልን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:26:19 0:00


XS
SM
MD
LG