በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ ለኤምፖክስ የተጋለጡ ወደ 4ሺ ሰዎች ተመዘገቡ


በሙንጊ፣ ኮንጎ በሚገኝ ክሊኒክ ህክምና የሚጠባበቅ ጎልማሳ።
በሙንጊ፣ ኮንጎ በሚገኝ ክሊኒክ ህክምና የሚጠባበቅ ጎልማሳ።

የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል ባለፈው ሳምንት በአህጉሪቱ ወደ 4,000 የሚጠጉ ለኤምፖክስ የተጋለጡ አዳዲስ ሰዎች መመዝገባቸውና ወረረሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን አስታወቀ፡፡

ማዕከሉ በወረረሽኙ እጅግ ወደተጎዳችው ኮንጎ የተላከው የመጀመሪያው ዙር ክትባት በመዘግየቱ አስፈላጊ ክትባቶች በአፋጣኝ እንዲሰጡ በድጋሚ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

በአፍሪካ ባለፈው ሳምንት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ 81 ሰዎች ሞተዋል፡፡ ይህ ቀደም ሲል የነበረውን የሟቾች ቁጥር ወደ 622 ከፍ ያደረገው ሲሆን ለወረርሽኙ የተጋለጡና የሞቱት ሰዎች ድምር 22,863 ደርሷል፡፡

የወረረሽኙ መናኻሪያ ናት በተባለችው ኮንጎ የቫይረሱ አዲስ ዝርያ በመታየቱ ችግሩን የበለጠ አሳሳቢ ማድረጉ ተዘግቧል፡፡

ከኮንጎ በተጨማሪ በጎረቤት ብሩንዲ ባለፈው ወር ለወረርሽኙ የተጋለጡ ወደ 800 የሚጠጉ ሰዎች ተመዝግበዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት ስርጭቱን ለመግታት የጤና እና የንፅህና አጠባበቅ እርምጃዎችን እየወሰዱ ቢሆንም እነዚህ እርምጃዎች እንደ ኮንጎ ባሉ ግጭቶች በተከሰቱባቸውና በርካታ ተፈናቃዮች ባሉባቸው አካባቢዎች ተግባራዊ ለማድረግ አስቸጋሪ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG