በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮንጎ ብራዛቪል 21 ሰዎች በኤምፓክስ ቫይረስ መያዛቸውን አስታወቀች


በቀደመው ጊዜ " የዝንጀሮ ፈንጣጣ" በሚል መጠሪያው በሚታወቀው ተላላፊ በሽታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እየጨመረ ነው።
በቀደመው ጊዜ " የዝንጀሮ ፈንጣጣ" በሚል መጠሪያው በሚታወቀው ተላላፊ በሽታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እየጨመረ ነው።

በኮንጎ ብራዛቪል 21 ኤምፖክስ በተሸኘው ወረርሸኝ የተያያዙ ሰዎች መመዝገባቸውን የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር እሁድ ዕለት ለመንግስቱ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ጊሊበርት ሞኮኪ ፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሀገር 158 በሽታው እንዳለባቸው የተጠረጠሩ ሰዎችን ከዓመቱ መጀመሪያ አንስቶ መመዝገቧን ፣ 21 ያህሉ በሽታው እንዳለባቸው መረጋገጡን አስታውቀዋል ። በቅርብ ጊዜዎች የበሽታው ተጠቂዎች የተለዩት ሀሙስ ዕለት መሆኑ ተነግሯል ።


በቀደመው ጊዜ " የዝንጀሮ ፈንጣጣ" በሚል መጠሪያው በሚታወቀው ተላላፊ በሽታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እየጨመረ ነው። ቫይረሱ በእስያ እና አውሮፓም ጭምር የታየ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ የጤና አደጋ በሚል አውጆታል።

ቫይረሱ ከ15ቱ የኮንጎ ብራዛቪል ግዛቶች መካከል 5ቱ ውስጥ መከሰቱ ተዘግቧል። ከግዛቶቹ መካከል ደናማዎች ሳንጋ እና ላይኩዋላ ግዛቶች በዋነኝነት ተጠቅተዋል ።

አዲሱ የኤምፖክስ ዝርያ በዴምክራቲክ ኮንጎ የተዛመተ ሲሆን ፣ በዚህ ዓመት ብቻ 570 ያህል ሰዎችን ገድሏል ።

ሞኮኪ በኮንጎ ብራዛቪል ወረርሽኙ አስደንጋጭ እንዳልሆነ ቢናገሩም ፣ ሰዎች እጅን አዘውትረው መታጠብን የመሳሰሉ የመከላከያ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል ።

ኤምፖክስ ለብዙ አሥርተ ዓመታት የሚታወቅ ቢሆንም ፣ ክላድ 1 የተሰኘ አዲስ ይበልጥ ገዳይ እና ይበልጥ የሚተላለፍ ዝርያ በቅርቡ ቁጥሩ ለጨመረው ተጠቂዎች ቁጥር መንስሄ እንደሆነ ተነግሯል ። ። ዘገባው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ነው ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG