No media source currently available
በትግራይ ክልል በራያ አላማጣ ወረዳ የገጠር ቀበሌ አስተዳዳሪዎች ለእርዳታ የተላከውን እህል ለማዳበርያ ክፍያ እንዲውል በጨረታ እየሸጡት ነው ሲሉ ያከባቢው ነዋሪዎች ይከሳሉ። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገብረእግዝአብሔር ወልደገብርኤል የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸው መረጃው እንደደረሳቸው ገልፀው፤የገጠር አስተዳዳሪዎችን ጠይቀው ድርጊቱ አለመፈፀማቸውን እንደነገርዋቸው ገልፀዋል።