ዶ/ር ቃለአብ ግርማ በወረቀት ተወስኖ የቆየውን የኢትዮጵያ ውስጥ የህክምና ማህደር አያያዝ ወደ ዲጂታል አማራጭ ለመለወጥ እየሰራ የሚገኘው "ሜዲኬት" ድርጅት መስራች ነው። ወጣቱ የህክምና ባለሙያ ከዘንድሮዎቹ የማንዴላ ዋሺንግተን የወጣት መሪዎች የትስስር መርሐ-ግብር ተሳታፊዎች አንዱ ነበር ። በዩናይትድ ስቴትስ ስላሳለፋቸው የልምድ እና ዕውቀት ሽግግር ሳምንታት ሀሳቡን አጋርቶናል ።
ኩልሱም ኑር፥ በኢትዮጵያ፣ የሕፃናት እና ሴቶች መብትን የሚመለከቱ ሕግ ነክ ምርምሮችን ያደረገች ባለሞያ ናት። ከሕግ ባለሞያነቷ ጎን ለጎን፣ በልዩ ልዩ ብዙኀን መገናኛዎች አበርክቶዋ፣ ማኅበረሰባዊ ንቃትንና ግንዛቤን ለማዳረስ ትጥራለች። ከዘንድሮዎቹ፣ የማንዴላ ዋሺንግተን "ያሊ 2023" የወጣት መሪዎች ትስስር መርሐ ግብር ተሳታፊዎች መካከል አንዷ የነበረችው ወጣት፣ በሚቺጋን ስቴትስ ዩኒቨርስቲ፣ የቀለም ትምህርት እና አመራር ሥልጠናዎችን ለሳምንታት ወስዳለች።
ወጣቱ የህክምና ባለሙያ ማቲያስ አማረ ከዘንድሮው የማንዴላ ዋሺንግተን የወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች የትስስር መርሐ-ግብር ተሳታፊ ኢትዮጵያን መካከል አንዱ ነው። የዘረጋቸው ህብረተሰብ አገዝ የህክምና መርሐ ግብሮች ርባና ተመዝኖ ለዚህ ዕድል የበቃው ዶ/ር ማቲያስ ፣ በአሜሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ስለነበረው የስልጠና እና የትስስር አፍታ ሀሳቡን አጋርቶናል ። ፋይሉ ከስር ተያይዟል ።
ጋቢና ቪኦኤ የአዲሱ ትውልድ ድምፅ በአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ክፍል ተዘጋጅቶ በየቀኑ ለ30 ደቂቃ የሚቀርብ የወጣቶች መርኃግብር ነው፡፡ በየቀኑ በኢትዮጵያዊያን ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2፡00 እስከ 2፡30 ይቀርባል፡፡