የአፍሪካ የፍልሰተኞች ፍሰት ገፅታ ብዙውን ጊዜ በትክክል እንደማይገለጽ የአፍሪካ ህብረትና ዓለማቀፍ የፍልሰት ድርጅት ያወጡት አብይ ዘገባ ያመለክታል። አብዛኞቹ አፍሪካውያን ፍልሰተኞች ባህሮቻችንና ውቅያኖሶችን በብልሹ ጀልባዎች ለማቋረጥ የሚሞክሩ ሳይሆኑ የአፍሪካን ድንበሮች በየብስ የሚሻገሩ ናቸው ይላል ዘገባው። የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ሳይመን ማርክስ ከአዲስ አባባ የላከው ዘገባ ዘርዝሩን ይዟል።
ከቅርብ ወራት ወዲህ ሊባኖስ በተለያየ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። ህዝባዊ አመፆች፣ የኢኮኖሚ ቀውስና አሁን ደግሞ በኮሮና ምክንያት የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ አገሪቱን አስጊ ሁኔታ ውስጥ ከቷቷል። በዚህም ምክንያት ከተለያየ የዓለም ክፍል የመጡ በመቶዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ስደተኞች ችግር ላይ ወድቀዋል፣ በሊባኖስ ጎዳና ላይ የሚወድቁትም ስደተኞች ቁጥር ቀን በቀን እየጨመረ ነው። ጃኮብ ራስል ከቤሩት የላከውን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ አጠናቅራዋለች።
ሊባኖስ ውስጥ የነበሩ 337 ኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልጋቸው የጉዞ ሰነድና ማስረጃዎች ተመቻችተውላቸው ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ።
ሞዛንቢክ ላይ የጭነት መኪና ጀርባ ባለ ኮንቴይነር ውስጥ ተቆልፎባቸው ለሞት ከተዳረጉት 64 ኢትዮጵያውያን መካከል በህይወት የተርፉት 11 ሰዎች ባለፈው አርብ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ሲሞን ማርክስ ከአዲስ አበባ ያደረሰንን ሪፖርት ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።
ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሎ ጀገንፎይ የተመለሱ አንዳንድ ተፈናቃዮች ለስድስት ወራት ድጋፍ ስላላገኘን ለችግር ተጋልጠናል ሲሉ ተናገሩ።
በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የሀገሩ መንግሥት የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠር ባሳለፈዉ ውሳኔ ምክንያት የዕለት ጉርስ ለማግኘት እየተቸገሩ መሆቸውን ተናግረዋል። መንግሥት ማንም ከቤቱ እንዳይወጣ ባሳለፈው ውሳኔ ከእጅ ወደ አፍ ኑሮን የሚገፉ ስደተኞች ቤተሰቦቻቸውን የሚመግቡት አጥተው ለረሃብ መጋለጣቸውን ለአሜርካ ድምፅ ገልፀዋል። የመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም በትውልደ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ላይ እገታ መብዛቱን ይናገራሉ።
ቤቲ ጂ በተለያዩ የሙዚቃ ስራዎቿ ትታወቃለች፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜም ዓለም አቀፍ እውቅና እያተረፈች የምትገኝ ወጣት ሙዚቀኛም ናት፡፡ በባለፈው ሳምንት ታዲያ፤ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞቸ ጉዳይ ኮሚሽን የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟታል፡፡ ኤደን ገረመው ከቤቲ ጂ ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርጋለች፡፡
በደቡብ ወሎ በኩል ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሃገሮች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሊሸጋገሩ የነበሩ ቁጥራቸው ወደ አንድ ሺህ የሚሆን ሰዎች ተይዘው ወደ የተነሱባቸው አካባቢዎች እንዲመለሱ መደረጉን የዞኑ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታውቋል። ወደ አረብ ሃገሮች ለመሸጋገር ሲሞክሩ የተያዙት ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ወጣቶች መሆናቸውን መምሪያው ያለፉ አምስት ወራት እንቅስቃሴውን አጣቅሶ በሰጠው መግለጫ ላይ አመልክቷል።
ሜዲቴራኒያን ባሕርን ሊያቋርጡ የነበሩ አርባ የሚሆኑ ሰዎች ትናንት /ማክሰኞ/ መስጠማቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር አስታወቀ። ሰዎቹ የተነሱት ከሊብያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ በስተምሥራቅ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኝ አል-ኾምስ ከተማ ነበር።
ከትግራይና ከሌሎችም አካባቢዎች ተሰድደው ቀይ ባሕር በማቋረጥ ላይ ከነበሩ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች የተሣፈሩባት ጀልባ ባለፈው ሣምንት በመገልበጧ ከአርባ በላይ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ሰጥመው መሞታቸውና ቤተሰቦቻቸውም መርዶው እንደተነገራቸው ተገለፀ።
ሲ- አይ (Sea-Eye) የተባለው የጀርመን የሰብዓዊ ደርጅት ቡድን በሊብያ ጠርፍ ከአደጋ ያተረፋቸውን 64 ፍልሰተኞች ለስድስት ቀናት ያህል ማረፍያ ወደብ ፍለጋ ሲዘዋወር በቆየው የመድህን መርክብ ውስጥ ሰንብተዋል።
ከሊቢያ የጠረፍ አደጋ ፍልሰተኞችን ያተረፈው የመድህን መርክብ ማቆሚያ ወደብ ፍለጋ ሲዘዋወር፤ 64 ከአደጋ የተረፉ ፍልሰተኞች የመጠጥ ውሀና የምግብ እጥረት እንደገጠማቸው የመርከቡ ባለሥልጣኖች አስታወቁ።
የአፍሪካ ኅብረት 32ኛ የመሪዎች ጉባዔ ስደትን ከምንጩ ለማድረቅ መስማማቱን አስታውቋል። ስደትና መፈናቀል ከአፍሪካ ሃገሮች ግንባር ቀደም ፈተናዎችም አንዱ ነው ተብሏል።
”እያገባደድን ባለነው 2018ዓም ብቻ ቁጥራቸው ከሦሥት ሺህ አራት መቶ በላይ የሚደርስ ሰዎች ለሕልፈት ተዳርገዋል።” ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት IOM
በዓለማችን ዙሪያ የሚገኙ ወጣት የእግር ኳስ ተጫዋቾች፣ ጀግና የሚሏቸው ኮከብ ተጫዋቾች የደረሱበት ትልቅ ደረጃ የመድረስ ተስፋ ሰንቀው ወደ አውሮፓ በመጓዝ እንደ ባርሴሎና ላሉ ታዋቂ ቡድኖች ለመጫወት ይፈልጋሉ። በዚህ ረገድ፣ አብዛኞቹ ከአፍሪካ የሆኑ ፍልሰተኞች የመጀመሪያውን ዕርምጃ ወስደዋል። በአንድ አዛኝ አሰልጣኝ ዕርዳታ አማካይነትም አፍሪካውያኑ ወጣቶች በስፔኑ ሊግ ውስጥ ቡድን መሥርተዋል።
በሊቢያ የእርስ በእርስ ጦርነት እየተባባሰ በመምጣቱና ያለጠባቂ በመተዋቸው ምክንያት ግንብ ንደው ከመጠለያው እንዳመለጡ 30 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለቪኦኤ ገለፁ። ከጦርነት ቀጠና ሸሽተው አሁን ያሉበት ቢደርሱም በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በፍጥነት ወደ ሃገራችን እንዲመልሰን እንማፀናለንም ብለዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ስደተኞቹን ወደ ሃገር ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ገልፀዋል።
ሊቢያ በሚገኘው አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ዩ ኤን ኤ ች ሲ አር (UNHCR) የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በከፍተኛ ረሃብ፣ በሽታና ህመም ላይ እንደሚገኙ ለቪኦኤ ገልፀዋል። ሊቢያውያኑ የጥበቃ ሰራተኞች ከስደተኞቹም የተወሰኑትን እየተለቀሙ እየወሰዱ እንደሆነና የሄዱበትንን ማንም እንደማያውቅ ጨምረው ገልፀዋል። ለደህንነታችን እንሰጋለን፣ ለባርነት ጠባቂዎቹ አሳልፈው እንደማይሸጡን ምንም ዋስትና የለንም ይላሉ።
አለም አቀፉን የስደተኞች ቀን ለማክበር ቀናቶች ሲቀሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰደተኞች በስፔን የባህር ወደብ ከተማ ደርሰዋል። በሶስት ጀልባዎች የተሳፈሩ 600 ስደተኞች የስፔኗ ቫለንቲካ ወደብ ከትላንት በስትያ ደርሰዋል። የደቡብ አውሮፓ ሀገራት ወደ ባህር ወደቦቻቸው የሚፈልሱ ቁጥራቸው የበዛ ስደተኞችን በተመለከተ መፍትሔ ለማበጀት ጥሪ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ትላንት ማምሻውን ከቱኒሲያ የባህር ወደብ አምስት ማይል ርቀት እንደተጓዘ ነው 180 ፍልሰተኞችን የጫነው ጀልባ የሰመጠው። እስከአሁን በጀልባዋ ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ 68ቱ ከሞት ተርፈዋል። 60 ፍልሰተኞች አስክሬን ተገኝቷል። የተቀሩት 52 ስደተኞችን ማፈላለጉ ቀጥሏል።
የማሊው ስደተኛ ማማዱ ጌሳማ ከአራተኛ ፎቅ ለመውደቅ የተንጠለጠለ የ4 አመት ህፃንን በሚያስገርም ፍጥነት ወደ ህንፃው ተንጠላሎ በመውጣትአድኗል። ከትላንት ጀምሮ ይህ በጎ ምግባሩ በአለም ዙሪያ በቴሌቭዥንና ሬድዮ ዘገባዎች እንዲሁም በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን በሰፊው እየተሰራጨ ነው።የፈረንሳዩ መሪ ኢማኑኤል ማርኮን ማማዱ ጌሳማ ለፈፀመው ጀብዱ የፈረንሳይ ዜግነትነት ሰጥተውታል። የቪኦኤ የባምባራ ዝግጅት ክፍል ወጣቱን አነጋግሮት ነበር፤ወደ አማርኛ መልሰን አቅርበንላችኃል።
የአስራኤል መንግስት ወደ ሃገሪቱ የገቡትንና ያለ ፈቃድ እየኖሩ የሚገኙትን አፍሪካውያን ስደተኞች በግዳጅ ለማስወጣት ያወጣውን ትዕዛዝ ትላንት ሰርዟል። በተለይም የእስራኤል መንግስት ወንድ ኤርትራውያንና ሱዳናውያን ስደተኞች ያለፍላጎታቸው ወደ ሌላ ሶስተኛ የአፍሪካ ሃገር ለመላክ ያስቀመጠውን ህግ በእስራኤል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
ስደተኞችን የሚመለከተውን የእስራኤልን ህግ በመቃወም ከሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎች በቴላቪቭ አቅራቢያ ቅዳሜ ምሽት ለሶስተኛ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያንና ሱዳናውያን ወደ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ በ3 ወር ጊዜ እስራኤልን ለቀው እንዲወጡ ሃገሪቱ ትዕዛዝ ካስተላለፈች 2 ወራት ተቆጥረዋል።በእስራኤል ሆሎት የስደተኛ ማቆያ ጣቢያ ከሚገኙት ኤርትራውያን ስደተኞች መካከል አንዱ ተከስተ የማነህ ስለሰላማዊ ሰልፉ በአጭሩ ገልጾልናል ።
ሄርዘሊያ በተባለችው የእስራኤል ከተማ በተደረገው በዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተዋል። የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥገኝነት የጠየቁ በርካታ ኤርትራውያንና ሱዳናውያን ስደተኞች ወደ መጡበት ሃገር ወይም ስደተኞቹን ለመቀበል ወደተስማሙ ሁለት የአፍሪካ ሃገሮች /ሩዋንዳና ኡጋንዳ/ በ3ወር የጊዜ ገደብ እንዲሄዱ የእስራኤል መንግስት ወስኗል። ካልሆነ ግን ስደተኞቹ ለእስር ይዳረጋሉ። ተከስተ የማነ ከኤርትራውያን ስደተኞቹ መካከል አንዱ ነው።
ተጨማሪ ይጫኑ