በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የስፓኝ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች የ73 ፍልሰተኞችን ሕይወት አዳኑ

የስፓኝ የባሕር ጠረፍ ጥበቃ አገልግሎት ሠራተኞች ትላንት ኅሙስ ከእንጨት በተሠራ ጀልባ ተሳፍረው በካናሪ ደሴቶች ላይ ይጓዙ የነበሩ 73 ስደተኞችን ህይወት አድነዋል።

ከሥፍራው የተገኙት የቪዲዮ ምስሎች፣ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎቹ የእንጨት ጀልባዋን ጎትተው ግራን ካናሪያ ደሴት ላይ ወደሚገኘው የአርጊንጊን ወደብ ከወሰዱ በኋላ፣ የተወሰኑ ጉዳት የደረሰባቸውን ፍልሰተኞች እና አንድ ሕፃን ሲረዱ አሳይተዋል።

በተያዘው የአውሮፓውያኑ 2024 ዓም ከጥር 1 እስከ መጋቢት 31 ባለው ጊዜ ውስጥ አደገኛውን የባሕር ጉዞ አልፈው ወደብ ላይ የደረሱ ሰዎች ቁጥር 13 ሺሕ 115 ሲደርስ፣ ይህም አሃዝ 2 ሺሕ 178 ፍልሰተኞች ከተመዘገቡበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ጭማሬ ማሳየቱን የስፓኝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የአውሮፓ ኅብረት የድንበር ጉዳዮች ድርጅት ፍሮንቴክስ እንዳስታወቀው፣ በአትላንቲክ ባሕር አድርጎ ወደ ካናሪ ደሴቶች የሚወስደው የባሕር መስመር በአሁኑ ወቅት ፍልሰተኞች ከምዕራብ አፍሪካ ተነስተው ወደ አውሮፓ ኅብረት አገሮች ለመግባት በሚያደርጉት ጉዞ ዋናው እና በርካታ ጉዞዎች የሚደረግበት መንገድ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG