በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትግራይን እያስተዳድሩ ያሉ ኃይሎች የኢትዮጵያ ወታደሮችን መልቀቃቸውን ገለፁ


(ፎቶ ፋይል፥ በትግራይ የታጠቁ ኃይሎች መቀሌን ከተቆጣጠሩ በኋላ ማክሰኞ , June 29, 2021)
(ፎቶ ፋይል፥ በትግራይ የታጠቁ ኃይሎች መቀሌን ከተቆጣጠሩ በኋላ ማክሰኞ , June 29, 2021)

ትግራይ ክልልን እያስተዳደሩ ያሉ ኃይሎች ይዘዋቸው የነበሩ 1,000 የመንግሥት ወታደሮችን መልቀቃቸውን የሕወሓት መሪ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በሳተላይት ስልክ እንደተናገሩ ሮይተርስ ዘገበ።

ወታደሮቹ በደቡብ ትግራይ ከአማራ ክልል ጋር ወደሚያዋስን አካባቢመሸኘታቸውን ዶ/ር ደብረ ጽዮን ቢናገሩም ወታደሮቹን የመልቀቁን ድርድር እንዴት እንደተካሄደና ማን እንደተቀበላቸው እንዳልነገሩትየዜና አገልግሎቱ አመልክቷል።

ከአምስት ሺሕ በላይ ወታደሮች አሁንም በእጃቸው እንደሚገኙ፣ በእጃችን አሉ የሚሏቸው ከፍተኛ የጦርአዛዦችን እንደማይለቁና ለፍርድ እንደሚያቀርቧቸው መግለፃቸውን ሮይተርስ አክሎ ዘግቧል።

ከኢትዮጵያ መከላከያ ኃይሎች ቃል አቀባይእና ትግራይን በሚመለከት ከተቋቋመው ግብረ ኃይል እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራእንዳልተሳካለት የጠቆመው ሮይተርስ የአማራ ክልል አስተዳደር ቃል አቀባይ ግን መረጃ እንደሌላቸው መናገራቸውን ገልጿል።

XS
SM
MD
LG