በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞችን ያሳፈረው መርከብ ሲሲሊ ወደብ ደረሰ


ከሜድትራኒያን ባህር የፍልሰተኞችን ህይወት አትርፎ እና አሳፍሮ ባህሩ ላይ ሲጠባበቅ የቆየው የጀርመን የሰብዓዊ ርዳታ መርከብ ጣሊያን ሲሲሊ ትራፓኒ ወደብ ደረሰ
ከሜድትራኒያን ባህር የፍልሰተኞችን ህይወት አትርፎ እና አሳፍሮ ባህሩ ላይ ሲጠባበቅ የቆየው የጀርመን የሰብዓዊ ርዳታ መርከብ ጣሊያን ሲሲሊ ትራፓኒ ወደብ ደረሰ

ከስምንት መቶ በላይ ፍልሰተኞችን ከሜድትራኒያን ባህር ህይወታቸውን አትርፎ፣ አሳፍሮ ባህሩ ላይ ሲጠባበቅ የቆየው የጀርመን የሰብዓዊ ርዳታ መርከብ ከጣሊያን ባለሥልጣናት ፈቃድ አግኝቶ ሲሲሊ ወደብ መድረሱ ተገለጸ።

ሲአይ የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት ያሰማራው ሲአይፎር የተባለው መርከብ ከትናንት በስቲያ ምዕራብ ሲሲሊ ትራፓኒ ወደብ ገብቷል። አብዛኞቹ አዋቂዎቹ ፍልሰተኞች ለጥንቃቄ ለኮቪድ-19 ማቆያ ወደተመደበ መርከብ የሚዛወሩ ሲሆን ከአንድ መቶ ስድሳ በላይ የሚሆኑ ህፃናት ደግሞ የብሱ ላይ ወዳሉ ወደመጠለያዎች እንደሚገቡ ተገልጿል።

የጀርመኑ ነፍስ አድን መርከብ ላይ ከነበሩት ፍልሰተኞች መካከል ግማሽ የሚሆኑት በወሩ መጀመሪያ ላይ እየሰጠመ ከነበረ የእንጨት ጀልባ ላይ የተደረሰላቸው ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ በተለያዩ የነፍስ አድን መርከብ እንቅስቃሴዎች የተደረሰላቸው መሆናቸው ተመልክቷል።

የጀርመኑ መርከብ ያሳፈራቸው አብዛኞቹ ፍልሰተኞች የምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች እንዲሁም የግብጽ ወይ የሞሮኮ ተወላጆች በጣሊያን የህጻናት አድን ድርጅት ባለሥልጣኑ ጂዮቫኒ ዲ ቤኔዲቶ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሦስት መቶ ስምንት ፍልሰተኞችን ያሳፍረው ኦሽን ቫይኪንግ የተባለው መርከብ ከሲሲሊ በስተደቡብ የምትገኘው ላምፔዱሳ ወደብ ለመግባት አሁንም ፈቃድ እየጠበቀ መሆኑ በዘገባው አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG