ደራሽ እርዳታ እየተሰጠ ያለበትን ጨምሮ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የተጓዘው አካባቢዎቹ ዘጋቢያችን የተመለከተው ከተከታዩ ዘገባ ያዳምጡ።
እውቁ ተዋናይ እና ጸሐፌ ተውኔት ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ በ84 ዓመታቸው አረፉ። ተስፋዬ ገሰሰ በኢዮጵያ ዘመናዊ የመድረክ ትወናን ካስተዋወቁት ቀዳሚ ተጠሪዎች መካከል እንደነበሩ ይታወቃል። መለስካቸው አመሐ ዘገባ አለው።
ማይካድራ ውስጥ በመቶዎች ሲቪሎች ላይ ጭፍጨፋ ለመካሄዱ ማስረጃ እንዳለው አምነስቲ አስታወቀ።ድርጊቱ በትግራይ የፀጥታ ኃይሎች ስለመፈፀሙ መረጃዎች ያመለክታሉ ሲል ያነጋገራቸውን እማኞች ቃል ጠቅሶ በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል።የትግራይ ክልል በትግራይ ሕዝብ ላይ የተጀመረው ከባድ የዘር ማጥፋት ወረራን ለመቀጠል ሆን ተብሎ የተሰራጨ የሐሰት ዜና ነው ብሎታል። በአካባቢው የነበረ የህወሃት ልዩ ሃይልና ሚሊሻ የፈጸመው ጅምላ ጭፍጨፋ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል:
ድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአስተዳደሩ ትምህርት ለማስጀመር አራት ዓይነት አማራጮችን ሊጠቀም ማሰቡን አስታወቀ። የአስተዳደሩ ትምሕርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የህጻናትን ደህንነት ባስጠበቀ መልኩ ትምህርት እናስጀምራለን ብለዋል። መግለጫውን የተከታተለው አዲስ ቸኮል ዝርዝር ዘገባ አለው።
በኢትዮጵያ በሕጻናት እና በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል እና በወላጆች ፣ በአሳዳጊዎች ፣ በመምህራን እንዲሁም በአጠቃላይ በኅብረተሰቡ ዘንድ ያለውን ንቃት ለመጨመር የሚያስችል ከለላ የተሰኘ መምሪያ በበጎ ፈቃደኞች ተዘጋጅቶ ለህዝብ ቀርቧል፡፡ ኤደን ገረመው የከለላ ለልጆች መስራች እና አዘጋጅ የተግባቦት ባለሞያ እና አማካሪ የሆነችውን ሰላም ሙሴን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡
ቤኒሻንጉል ጉምዝ ውስጥ 378 ሰዎች፤ ጋምቤላ ውስጥ ደግሞ 645 ሰዎች በኮቪድ 19 መያዛቸውን የክልሎቹ የጤና ቢሮዎች ኃላፊዎች ገልፀዋል።ጋምቤላ ውስጥ ሰባት ሰዎች በኮቪድ 19 ምክንያት መሞታቸው ተነግሯል።
የየመን ሁቲ አማጺያን በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከሀገራቸው ለማስወጣት በከፈቱት ተኩስ በርካታ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው ሂውማን ራይትስ ዎች ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የተኩስ ጥቃቱን ለማምለጥ ወደ ሳውዲ ድምበር ለመግባት የሞከሩ በርካታ ስደተኞች ላይ የሳውዲ ድምበር ጠባቂ ወታደሮች ተኩስ በመክፈታቸው ተጨማሪ ኢትዮጵያኖች መሞታቸውንም መግለጫው አካቷል።
የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እና በርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ ሃያ ሰዎች በ2 ሚሊዮን ብር ዋስ ተለቅቀዋል። በዋስ መለቀቃቸውን ተከትሎ ዞኑ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እየተመለሰ መሆኑን የዞኑ ነዋሪዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል።
እስራኤል እና የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች ግንኙነታ ለመቀጠል መስማማታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት አስታወቁ።ይህ ስምምነት የአብራሃም ውል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል እስራኤል እ ኤ አ በ 1948 ነጻ ሃገር ሆና ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ከዚህኛው በፊት ከአረቦች ጋር የሰላም ስምምነት ያደረገችው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው።
የክልሉ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ እንዳስታወቀው የኮረናቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ተብሎ የይቅርታ መምርያ የሚያሟሉ የህግ ታራሚዎች እንዲፈቱ ተወስኗል::
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መስፋፋት ከጀመረ አንስቶ እስካሁን ባለው ጊዜ እዚያ በስደተኛነት ይኖሩ የነበሩ ከአሥር በላይ ኢትዮጵያዊያን በበሽታው ምክንያት መሞታቸው ተነግሯል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በህብረተሰቡ ውስጥ በፈጠረው ፍራቻ ምክንያት የደም ለጋሾች ቁጥር እጅጉን ቀንሷል።ይህም በጤና ተቇማት ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት አስታውቇል። በተለይ ብስፋት የደምልገሳ ይካሄድባቸው የነበሩት ትምህርት ቤቶች መዘጋትና ከቫይረሱ ጋር ተያይዘው የወጡ መመሪያዎች ለደም ለጋሾችመመናመን አስተዋፅኦ አድርገዋል።
ለኮረና ቫይረስ ተጋልጠው ይሆናል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎች የሚወሰደው ናሙና እንዴት ይመረመራል? ውጤቱን ለማወቅስ ስንት ቀን ይወስዳል?
ለኮረና ቫይረስ ተጋልጠዋል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎችን ነጥሎ ማቆያ ጣቢያዎች ይዘት ምን ይመስላል? ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለሞያ ጠይቀን ያጠናቀርነውን ዘገባ ተከታተሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአቶ ጃዋር መሐመድን ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሁኔታን እንዲያረጋግጥ ቀነ ገደብ የተቀመጠለት ሁለተኛ ደብዳቤ ለኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጻፈ። ኦፌኮ በበኩሉ ጉዳዩ በሕጉ መሠረት እልባት እንዲያገኝ እናደርጋለን ብሏል። (ዝርዝሩን ያዳምጡ)
“ሰብዓዊ መብትትን የሚጥሱ ሰዎች ላይ ለምን እርምጃ ተወሰደ? የሚል ተቃውሞ ማሰማት እጅግ አሳዛኝ ነው” - አቶ ታዬ ደንዳአ
ለሶማሌ ሕዝብ ነጻነትና ዴሞክራሲ እንደሚታገል ያስታወቀው አዲሱ ፓርቲ ቅንጅት ለዴሞክራሲና ለነጻነት ይሰኛል። የፓርቲው መስራች ጉባዔ እስከስኞ ድረስ ይቀጥላል ተብሏል። ፓርቲው ዋና መቀመጫውን በጅግጅጋ እንደሚያደርግና በድሬዳዋና አዲሰበባም ቅርንጫፎች እንደሚኖሩት ገልጿል።
ባለፈው ቅዳሜ በቦረናና በምስራቅ ጉጂ ስድስት ሰዎች በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሸማቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። ከመካከላቸው የፀጥታ ጠባቂ ሚሊሺያዎችና ነዋሪዎች እንዳሉባቸው የአካባቢው አስተዳደር ገልጿል።
ኢትዮጵያ ለስደተኞች መጠለያ ከመሆን ጎን ለጎን ስደተኞቹ እንደ ማንኛውም ዜጋ መብታቸው ተከብሮ በሀገሪቱ ውስጥ እንዲኖሩ እና ሠርተው መኖር እንዲችሉ ቅድመ ሁኔታዎች እየተመቻቹ ነው ሲል የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ገልጿል። ኤጀንሲው ዛሬ በአዲስ አበባ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተዋል።
ከፈረሰው የሰገን አከባቢ ሕዝቦች ዞንና ከመዋቅር ጥያቄ ጋር በተገናኘ በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 20 ሰዎች መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ግጭቱ የተፈጠረው በወረዳ በነያ በተሰኘ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሲሆን መንስኤው የመዋቅር ጥያቄ መሆኑን ነዋሪዎች ለቪኦኤ በስልክ ተናግረዋል። የሃዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ ተጨማሪ ሪፖርት ልኮልናል።
የሶማሌ ክልል መንግሥት ከአፋር ክልል በሚነሱ ታጣቂዎች ጥቃት ካለፈው ታኅሣሥ ጀምሮ ከ270 በላይ ንጹሀን ዜጎች ተገድለዋል አለ። ባለፈው ቅዳሜ ተከስቶ በነበረው ግጭትም ከ30በላይ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በሦሥት ቦታዎች መገደላቸውን ገልጿል። የሲቲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዑመር አብዲ የመገናኛ ብዙሃን ሚዛናዊ ዘገባ እያቀረቡ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል። በተያያዘ በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ልዩ ልዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።
ተጨማሪ ይጫኑ