ገንዘቤ ዲባባና ዮሚፍ ቀጄልቻ በፖርትላንድ ድል ተቀዳጁ

  • ሰሎሞን ክፍሌ

ኤዲ ኢዛርድ የተባለ የ 54 ዓመት ኮሜዲያን፥ 27 ማራቶኖችን በ 27 ቀናት ውስጥ ሮጧል (አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)

የዛሬው ሳምንታዊ የስፖርት ፕሮግራም፣ ኤዲ ኢዛርድ የተባለ የ 54 ዓመት ኮሜዲያን፥ 27 ማራቶኖችን በ 27 ቀናት ውስጥ እንደሮጠ፣ እና የኢትዮጵያ አትሌቶች በመጪው ግንቦት ዩጂን ኦሪጎን በሚካሄደው የዳያመንድ ሊግውድድር ለመሳተፍ ተመልሰው እንደሚመጡ ይጠበቃል።

በፖርትላንዱ የዓለም አዳራሽ ውስጥ ሻምፒዮና ውድድር በሴቶቹ 3,000 ሜትር ውድድር አሸናፊዋ ልማደኛዋ ገንዘቤ ዲባባ እንደምትሆን ሳይታለም የተፈታ ነበር።

በተመሳሳይ ርቀት የወንዶቹን ድል የተቀዳጀው ደግሞ ወጣት ዮሚፍ ቀጄልቻ ነው። ሁለቱም በየግላቸው ያስመዘገቧቸው ሰዓቶችም የሚናቁ አልሆኑም፥ የገንዘቤ 8 ደቂቃ ከ 47 ነጥብ4 - 3 ሴኮንድ ሲሆን የዮሚፍ 7 ደቂቃ ከ 57 ነጥብ 2 - 1 ሴኮንድ ሆኗል።

ሁለቱም የኢትዮጵያ አትሌቶች በመጪው ግንቦት ዩጂን ኦሪጎን በሚካሄደው የዳያመንድ ሊግውድድር ለመሳተፍ ተመልሰው እንደሚመጡ ይጠበቃል።

ኤዲ ኢዛርድ የተባለ የ 54 ዓመት ኮሜዲያን፥ 27 ማራቶኖችን በ 27 ቀናት ውስጥ ሮጧል።

አርቲስቱ ይህን ያደረገው ኔልሰን ማንዴላ የመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዘዳንትከመሆናቸው በፊት ለ 27 ዓመታት በእሥር መቆየታቸውን ለማስታወስ ነው ተብሏል።

አስቂኙ አርቲስት በጠቅላላው የሮጠው 707 ማይሎችን ሲሆን በውሃ ጥም ማረሩና ቆዳው መቆሳሰሉተስተውሏል። ኤዲ ኢዛርድ አጋጣሚውን የስፖርት ፕሮግራሞችን ለማስፋፊያ ገንዘብ ማሰባሰቢያነትም ተጠቅሞበታል።

በእለቱም ከደጋፊዎቹ ከአንድ ሚሊዮን ፓውንድ በላይ መሰብሰብ ችሏል።

ሰሎሞን ክፍሌ ዝርዝሩን አጠናቅሮ አቅርቦታል፣ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል በመጫን ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ገንዘቤ ዲባባና ዮሚፍ ቀጄልቻ በፖርትላንድ ድል ተቀዳጁ

Your browser doesn’t support HTML5

ገንዘቤ ዲባባና ዮሚፍ ቀጄልቻ በፖርትላንድ ድል ተቀዳጁ