በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ አትሌቶች ድል ተቀዳጁ


ኢማነ መርጋ የወንዶችን 5000 ሜትር የብራስልስ ማራቶን እአአ 2011 ሲወዳርደር
ኢማነ መርጋ የወንዶችን 5000 ሜትር የብራስልስ ማራቶን እአአ 2011 ሲወዳርደር

የኢትዮጵያ አትሌቶች በተለያዩ የዓለም ከተሞች በተካሄዱ የረዥም ርቀት ሩጫ ውድድሮች ድል ተቀዳጁ።

ኢማነ መርጋ እና በላይነሽ ኦልጂራ በስፔን ዓለምአቀፍ አገር አቋራጭ፥ አፀደ ባይሣና አማኔ ጎበና በጃፓንና ቱርክ ማራቶኖች አሸንፈዋል። ኢማነ መርጋ በዚህ ውድድር ሲያሸንፍ ትላንት በተከታታይ ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑ ተደናቂ አድርጎታል።

በእግር ኳስ - የአፍሪካ ብሄራዊ ቲሞች ለ 2018ቱ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሚያደርጉት የማጣሪያ ውድድር በሣምንቱ ማብቂያ ቀናትም ቀጥሏል። ቅዳሜ እለት አዲስ አበባ ላይ የኮንጎ ብራዛቪል ቡድን የኢትዮጵያ ዋሊያዎችን 4 ለ 3 አሸንፎ ተመልሷል።

እሥራኤል ዘጠኝ ሺህ ለሚሆኑ የኢትዮጵያ አይሁዶች የመግቢያ ፈቃድ እንዲሰጥ ወሰነች። የኢትዮጵያ አይሁዶች፥ ”ፈላሻ” “ፈላሽ ሙራ” እና ”ቤተ-እሥራኤላውያን” በመባልም ይታወቃሉ። ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ አትሌቶች ድል ተደዳጁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:33 0:00

XS
SM
MD
LG