ዑመር ዘ ቸቸን የተባለ እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ጽንፈኛ ቡድን ከፍተኛ መሪ እንደሞተ ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች

ፋይል ፎቶ - ዑመር ዘ ቸቸን የተባለ እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ጽንፈኛ ቡድን ከፍተኛ መሪ

ዑመር ዘ ቸቸን የተባለ እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ጽንፈኛ ቡድን ከፍተኛ መሪ በደረሰበት ጉዳት እንደሞተ ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች።

ዑመር ዘ ቸቸን የተባለ እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ጽንፈኛ ቡድን ከፍተኛ መሪ በደረሰበት ጉዳት እንደሞተ ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች። የቆሰለውም አሜሪካ ከአንድ ሳምንት በፊት እሱን ኢላማ በማድረግ ባካሄደችው የአየር ድብደባ እንደሆነ ገልጻለች።

የዩናይትድ ስቴትስ የመካለከያ ሚኒስቴር ባለስልጣኖች ዑመር ዐል-ሺሻኒ ጂሐዳውያኑ ስብሰባ ላይ እንዳሉ በተከፈተው ጥቃት ከሌሎች 12 የቡዱኑ አማጽያን ጋር ተገድሏል ብለው ነበር። ኋላ ደግሞ እንደተረፈ ጠቁመው ትላንት እንደሞተ ተናግረዋል።

የሟቹ ስም ታርካን ባቲራሽቪሊ (Tarkhan Batirashvili) ሲሆን ሺሻኒ የአመጽ ስሙ ነው። ከጽንፈኛው ቡድን ከፍተኛ ብቃት ያላቸው ወታደራዉ አዛዦች አንዱ እንደነበር ታውቋል።

ዩናይትድ ስቴትስ እሱን ላስያዘ ሰው የአምስት ሚልዮን ዶላር ሽልማት እንደምትሰጥ አስታውቃ ነበር። የአሜሪካ ባለስልጣኖች እንደሚሉት ለጂሃዳውያኑ በመከላከያ ሚኒስትርነት ደርጃ ይታይ ነበር።

እ.አ.አ. በ 2006 ዓ.ም. ከጆርጂያ ወታደራዊ ሃይል ጋር ተሰልፎ የሩስያ ሀይሎችን ከመዋጋቱ በፊት በቼቸን አማጺነት የሩስያ ወታደራዊ ሃይልን ተዋግቶ ነበር። በ2008 ዓ.ም. ደግሞ የሩስያ ወታደሮችን ይዋጋ ነበር። ከአራት አመታት በኋላ ሶርያ ሄዶ የባእዳን ተዋጊዎች ግብረ-ሃይል መሪ ሆነ።

እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ሃይል ሶርያ እንደገባም በሰሜን ሶርያ የጂሃዳውያኑ ወታደራዊ ሃይል መሪ ሆነ።