በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምላሽ፥ ለእስላማዊው ጽንፈኛው ቡድን አይስል የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ


ፋይል ፎቶ - የአይስል ታጣቂዎች በራቃ ክፍለ-ሃገር ሶርያ ውስጥ እ.አ.አ. 2014
ፋይል ፎቶ - የአይስል ታጣቂዎች በራቃ ክፍለ-ሃገር ሶርያ ውስጥ እ.አ.አ. 2014

"አይስልን 'ISIL' የመሳሰሉ ቡድኖች ትክክለኛ መስሎ ለመቅረብ የማያደርጉት የለም። ራሳቸውን ለእስልምና እንደ ቆሙ የሃይማኖት መሪዎች፤ የያዙትንም እንደ ቅዱስ ጦርነት አድርገው ለመሳል ይጥራሉ። ለመልካም ዓላማ የቆሙ ማስመሰያቸውን የሚያደርጉትን መፍቀድ የለብንም።"

እስላማዊው ጽንፈኛው ቡድን አይስል (ISIL) በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃንና በሌሎች የፕሮፖጋንዳ ማሰራጫዎቹ በሚያስተላልፋቸው መልዕክቶች አማካኝነት በብዙ ሺህ የሚገመቱ ተዋጊዎችን ይመለምላል።

የጉዳዩ አዋቂዎች እንደሚሉት ከሆነ የአሸባሪውን ቡድን የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶች ለማምከን የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ግዙፍና ዓይነተኛ ጥረት ይጠይቃል።

ሁሉም ለፍጹምነት የተቃረበ፤ ፍጹምነት የሰፈነበት እስላማዊ መንግስት ለመመሥረት ሙስሊሞች በሙሉ መሳተፍ አለባቸው፥ ይላል፤ ጽንፈኛው ቡድን አይስል (ISIL) በፍርሃት ቀስቃሽ ውዥንብርና ማስጠንቀቂያ በታጀበ ፕሮፖጋንዳው።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ለሙስሊም አሜሪካውያን ማኅበረሰብ ባደረጉት ንግግራቸው፤ በእንግሊዝኛው ምሕጻረ-ቃል አይስል (ISIL) እና ISIS በሚሉ መጠሪያዎች የሚታወቀው አሸባሪ ቡድን ስለሚያሰራጨው የሃሰት መረጃ አደገኛነት አሳስበዋል።

የዘገባውን ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ፤

ምላሽ፥ ለእስላማዊው ጽንፈኛው ቡድን አይስል የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:21 0:00

XS
SM
MD
LG