የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትናንትናውለት የጀመረው የዘጠና ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከ 700 ሚሊዮን ዶላርስ በላይ ለማሰባሰብ ያለውን እቅድ አስታውቋል።
አዲስ አበባ —
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 10.2 ሚሊዮን ዜጎችን ለተረጂነት ያጋለጠው ድርቅ፤ ያስከተለው ጉዳይ አነስተኛ ቢሆንም የዝናብ እጥረቱ ግን ከ1977ቱ የከፋ መሆኑን የእርዳታ ድርጅቶች በመግለጽ ላይ ናቸው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትናንትናውለት የጀመረው የዘጠና ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከ 700 ሚሊዮን ዶላርስ በላይ ለማሰባሰብ ያለውን እቅድ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት የበልግ ዝናብ በከፊል መጥፋትም የዜጎችን የምግብ ዋስትና ክፉኛ መፈታተኑን በአዲስ አበባ በመንግስታቱ ድርጅት የUN- OCHA ቃል አቀባይ ቾይዝ ኦኮሮ አስረድተዋል።
ከአንድ ወር በፊት ይጀምራል ተብሎ ተጠብቆ ለነበረው የበልግ ወቅት፤ ገበሬዎች ለመዝራት እንዲችሉ የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት 4ሚሊዮን ዶላርስ የሚያወጣ ዘር እንደሚያከፋፍል አስታውቆ ነበር። እስክንድር ፍሬው ዝርዝሩን ከአዲስ አበባ ልኳል።
Your browser doesn’t support HTML5