የያዝነው ዓመት እጅግ የከበደ ይሆናል

ባለፈው የአውሮፓ 2015 ዓ.ም ውስጥ ለደረሱት የተፈጥሮ አደጋዎች የአየር ንብረት ለውጥ እና የኤል-ኒኞ ክስተት አስተዋፅዖ ማበርከታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አዲስ የጥናት ሪፖርት አስታወቀ።

ባለፈው የአውሮፓ 2015 ዓ.ም ውስጥ ለደረሱት የተፈጥሮ አደጋዎች የአየር ንብረት ለውጥ እና የኤል-ኒኞ ክስተት አስተዋፅዖ ማበርከታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አዲስ የጥናት ሪፖርት አስታወቀ።

ክስተቱ በድርቆች፣ በጎርፎችና ሌሎችም ከአየር ጠባይ ጋር የተያያዙ በዓለም ዘሪያ በደረሱ አደጋዎች መስፋት፣ ብዛትና ብርታት ላይ ጫና ማሳደሩን ሪፖርቱ አመልክቷል።

በ2015 ዓ.ም ውስጥ በዓለም ዙሪያ 32 ግዙፍ የሚባሉ የድርቅ ክስተቶች እንደነበሩ የተባበሩት መንግሥታት የአደጋዎች መዘዝ መቀነሻ ቢሮ አስታውቋል።

ለወትሮ እንዲህ ዓይነት አደጋዎች በአሥር ዓመት አማካይ በዓመት አሥር እንደሚደርሱ ነው ተመዝግቦ የሚገኘው። የአምናው ግን ከአሥሩ ዓመት አማካይ ከእጥፉም በብዙ በልጦ ነው የታየው።

ከድርቆች የበዙት የደረሱትና የተጎዱት ደግሞ ከሰሃራ በስተደቡብ ያሉ አካባቢዎችን ነው።

ቤልጅግ የሚገኘው የተዛማች አደጋዎች ጥናት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዴባራቲ ጉሃ ሳፒር 2015 ዓ.ም የድርቅ ዓመት ነበር ሲሉ ጠርተውታል።

የያዝነው 2016 ዓ.ም ደግሞ አስፈላጊ እርምጃዎች ቀድመው ካልተወሰዱ የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የያዝነው ዓመት እጅግ የከበደ ይሆናል