የሶሪያ መንግስት በጦርነት ለተጎዱት የሰብአዊ እርዳታ እንዳይታደል ፈቃድ ከለከለ ሲሉ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለስልጣን አማረሩ።
ጀኔቫ —
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ አማካሪ ጃን ኤግላንድ (Jan Egeland) እንደገለጹት በጦርነት ቀጠና ዉስጥ ለሚገኙና ሊደረሰባቸዉ ከባድ የሆነ 287,000 ለሚሆኑ ሶሪያዉያን የእርዳታ ቁሳቁስ ለማድረስ ላለፉት አራት ቀናት ካገሪቱ መንግስት ፈቃድ ማግኘት አልተቻለም።
የሶሪያ ተቃዋሚዎችም የእርዳታ እህል እንዳያልፍ መንገድ እንደሚዘጉ ባለስልጣኑ የገለጹ ሲሆን ጦርነት ከሚካሄድባቸዉ አስራ ስምንት አካባቢዎች አስራ አምስቱ መንግስት ቁጥጥር ሥር ስለሚገኙ ዋናዉ ተጠያቂ መንግስት ነዉ ብለዋል።
ሰፋ ያለ ዝርዝር ባልደረባችን ሊሳ ሽላይን አጠናቅራ የዘገበችውን ትዝታ በላቸው አቅርባዋለች፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
የሶሪያ መንግስት በጦርነት ለተጎዱት እርዳታ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑ ተነገረ