የኮምሁሪየት (Cumhuriyet) ጋዜጣ ሪፖርተሮች ካን ዱናር እና ኤርደም ጋል ጥፋተኞች ከተባሉ በእድሜ ልክ እሥራት ሊቀጡ ይችላሉ ተብሏል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በቱርክ ዛሬ ሁለት በዘገባችሁ የመንግሥት ሚሥጥር አውጥታችሁዋል፥ አሸባሪ ድርጅት ረድታችሁዋል ተብለው የተከሰሱ ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
የኮምሁሪየት (Cumhuriyet) ጋዜጣ ሪፖርተሮች ካን ዱናር (Can Dundar) እና ኤርደም ጋል (Erdem Gul) ጥፋተኞች ከተባሉ በእድሜ ልክ እሥራት ሊቀጡ ይችላሉ ተብሏል።
እ. አ. አ. በ 2014 ወደ ሦሪያ ያመራል በተባለ የካምዮን ፎተግራፍ ታጅቦ በጋዜጠኞቹ የቀረበ ሪፖርት፥ ቱርክ የጦር መሣሪያ በድብቅ ለሦሪያ ማስተላለፏን ያረጋግጣል ይላል።
ጋዜጠኞቹ በዚያ ሪፖርታቸው፥ ተቀማጭነታቸውን በዩናይትድ ስቴትስ በማድረግ የእስላማዊ እንቅስቃሴ የሚመሩትን ፈትሁላ ጉለንን (Fethullah Gulen) ረድቷል ስትል ቱርክ በበኩሏ ታስረዳለች።