በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦባማ ለፈንድሻና ለከረሜላ ምሕረት አደረጉ


ኦባማ ለፈንድሻና ለከረሜላ ምሕረት አደረጉ
ኦባማ ለፈንድሻና ለከረሜላ ምሕረት አደረጉ

በአሜሪካ ዛሬ የምሥጋና ቀን ነው፡፡ የዚህ ዓመቱ የምሥጋና ቀን መንግሥታዊ ተርኪ ፓፕኮርን /ፈንድሻ/ መሆኗን ፕሬዚዳንት ኦባማ በይፋ አስታውቀዋል፡፡ /የተርኪዎቹ ስም ነው ፈንድሻና ከረሜላ/



ከረሜላና ፈንድሻ
ከረሜላና ፈንድሻ

please wait

No media source currently available

0:00 0:27:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በዋይት ሃውስ የተካሄደውን የምኅረት ሥነ-ሥርዓት ለማየት ይህንን ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ
http://www.whitehouse.gov/blog/2013/11/27/presidential-turkey-pardon-curious-if-humane-tradition

በአሜሪካ ዛሬ የምሥጋና ቀን ነው፡፡ የዚህ ዓመቱ የምሥጋና ቀን መንግሥታዊ ተርኪ ፓፕኮርን /ፈንድሻ/ መሆኗን ፕሬዚዳንት ኦባማ በይፋ አስታውቀዋል፡፡ /የተርኪዎቹ ስም ነው ፈንድሻና ከረሜላ/

አሜሪካዊያን ዕለቱን ቤተሰብና ጓደኛ በመጠያየቅ፣ በመሰባሰብ፣ የምሥጋና ቃላትን በመለዋወጥ፣ በምግብ፣ ለዕለቱ ተብሎ ዋጋቸው እጅግ ያሽቆለቆለ ሸቀጦችና ቁሣቁስ በመግዛት ያሣልፉታል፡፡ ዛሬንም በዚያው ልማድ መሠረት ይዘውታል፡፡

ተርኪ ተዘጋጅታ
ተርኪ ተዘጋጅታ
የዕለቱ ልዩ ምግብ የሆነችው ተርኪ ተጠብሣና በተለያዩ አድማቂና አሸብራቂ የምግብ ዓይነቶች፣ በጣፋጭና ተከታዮቿም ተሽሞንሙናና ታጅባ ነው የምትዘጋጀውና የምትቀርበው፡፡

ሜሲስ የሚባለው ግዙፉ የገበያ ኩባንያ ታላላቅ ታዋቂ ተዋንያንና ድምፃዊያንን እየያዘ የገበያ አዳራሾቹ በያሉበት ሰልፎችና ዝግጅቶችን እያከናወነ ነው፡፡

ከምሥጋና ቀን በፊት ያለው ቀን በዩናይትድ ስቴትስ ከዓመቱ ሁሉ ጉዞ በእጅጉ የበዛበት ዕለት ሲሆን በዚህ በያዝነው ሣምንት ውስጥ ብቻ በመላ ዩናይትድ ስቴትስ 43 ሚሊየን ሰው ሰማንያ ኪሎ ሜትርና ከዚያም በላይ እየተጓዘ መሆኑን የአሜሪካ የአውቶሞቢል ማኅበር ገልጿል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማም ትናንት ምግብ ሲያድሉ የዋሉ ሲሆን በልማዱ መሠረትም “ከሜኔሶታ ድረስ በጀግንነት ተጉዘው ዋይትሃውስ ለደረሱት ‘ፈንድሻና ከረሜላ’ /ካራሜል እና ፓፕኮርን/ ተብለው ለተሰየሙ ሁለት ተርኪዎች “በተሰጠኝ ሥልጣን መሠረት ለፓፕኮርን ከእንጆሪ ማጥቀሻ እና በቅመማ ቅመም ከመታጀልም ነፃ ትሆን ዘንድ ሙሉ ምኅረትን ሰጥቻለሁ፤ መልካሙን ሁሉ እንመኝልሻለን” ሲሉ ምኅረትን ቸረዋል፡፡ በሥፍራው ለተሰበሰበው ሁሉም፣ ለአሜሪካ ሕዝብ፣ በመላው ዓለም በግዳጅ ላይ ለሚገኙ መለዮ ለባሾቻቸው በግራቸውና በቀኛቸው ከቆሙ ልጆቻቸው ሳሻና ማልያ ጋር በመሆን በኦባማ ቤተሰብ ስም መልካሙን ተመኝተዋል፡፡

ለሁሉም ተርኪዎች ምኅረት እንዲደረግ ዋይት ሃውስ ደጅ ላይ ወጥተው የጠየቁ የተርኪ ልማድ ተቃዋሚዎች
ለሁሉም ተርኪዎች ምኅረት እንዲደረግ ዋይት ሃውስ ደጅ ላይ ወጥተው የጠየቁ የተርኪ ልማድ ተቃዋሚዎች
ፕሬዚዳንት ኦባማ ለፈንድሻና ለከረሜላ ምህረትን እያወጁ በነበሩበት ወቅት ለሁሉም ተርኪዎች ምኅረት እንዲደረግ ዋይት ሃውስ ደጅ ላይ ወጥተው የጠየቁ የተርኪ ልማድ ተቃዋሚዎች የቶፉ ተርኪ አማራጭ ይዘው ቀርበዋል፡፡

ከላይ የተያያዘው የድምፅ ፋይል የምሥጋና ቀንን ልዩ ዝግጅት ይዟል፤ ያዳምጡት፡፡
XS
SM
MD
LG