ዋሽንግተን ዲሲ —
የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይደር አል አባዲ (Haider al-Abadi)የቱርክ የጦር ሓይሎች ከኢራቅ በአስቸኩዋይ መውጣት ኣለባቸው ሲሉ በድጋሚ አሳሰቡ።
ቱርክ ወታደራዊ አሰልጣኝዎችዋን ስለምን ወደ ኢራቅ ድንበሮች አዝልቃ ትልካለች?የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይደር አል አባዲ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ረቡዕ ከቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትር አህመት ዳቩቶጉሉ (Ahmet Davutoglu)ጋር በቴሌፎን ሲነጋግሩ፣ "የእስልምና መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ተዋጊዎች ቱርክና ሶሪያ ድንበር ላይ ናቸው እየተባለ ቱርክ ወታደራዊ አሰልጣኝዎችዋን ስለምን ወደ ኢራቅ ድንበሮች አዝልቃ ትልካለች?” ሲሉ ጠይቀዋል። የዜና ዘገባችንን ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።