በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱርኩ ጠቅላይ ሚንስትር ለትላንቱ በወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰው የፈንጂ ጥቃት የሶሪያ ኩርድ ሚሊሻዎችን ተጠያቂ አደረጉ


አንካራ ላይ መንገድ ዳር የተቀበረው ፈንጂ ለሃያ ስምንት ሰዎች ሞት ምክኒያት መሆኑ ይታወቃል።

ከትላንቱ በሁለት የወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ ከደረሰ የፈንጂ ጥቃት ጀርባ ያሉት ፒ ዋይ ዲ(PYD) በሚል በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል የሚታወቀው የሶሪያ ኩርዶች ቡድንና ወታደራዊ ክንፉ ፒ ዋይ ጂ(YPG) መሆናቸውን የማያጠራጥር መረጃ የደህንነት ሠዎቻቸው ማግኘታቸውን ጠቅላይ ሚንስትሩ የተናገሩት።

"ፒ ዋይ ጂ(YPG)​ያደረሰው ይህ ጥቃት ለፒኬኬ ሚልሻዎች አስፈላጊ ድጋፍ በቱርክ ምድር ውስጥ የተፈጸመ ነው፤" ብለዋ።

የቱርክ የጸጥታ ሠራተኞች የቦምቡብን ጥቃት ከሶሪያውያኑ ጋር የሚያገናኝ የጣት አሻራ መረጃ ማግኘታቸውን ይናገራሉ።

ዳቩቶግሉ አክለውም፤ ዩናይትድ ስቴትስና አንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ከጽንፈኛው እስላማዊ ቡድን ጋር በሚያደርጉት ውጊያ ከሚደግፏቸው ሶሪያውያን ኩርዶች ጋር አገራቸው በምታካሂደው ውጊያ አብረዋቸው እንዲሰለፉ ሲሉ ጥሪ አቅርበውላቸዋል።

አንካራ ከኡን ቀደምም በድኑን በአሸባሪነት የምትፈርጀውን የቱርኩን የኩርዶች ቡድን ፒኬኬን (PKK) ይረዳል ስትል ትወነጅላለች።

የሶሪያ ኩርዶች ቡድን ፒ ዋይ ዲ(PYD)​መሪ ሳልህዑስሊም በትላንቱ ጥቃት ቡድናቸው የለበትም ሲሉ ውንጀላውን አስተባብለዋል።

የቱርክ የጸጥታ ኃይሎች ከፍንዳታው ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ያሰሯቸው ሰዎች መኖራቸው ተዘግቧል። በጉዳዩ ዙሪያ ለሚደረግ ግልጽና የተሟላ ምርመራ ዝግጁ ነኝ ያለው የቱርክ መንግስት፤ የጸጥታ ኃይሎቹን የቦምብ ጥቃቱን አያያዝ ጨምሮ ትችት በሚሰነዝሩ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ኣነሳለሁ፤ ሲል ቃል ገብቷል።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG