የታንዛኒያ ፍርድ ቤት 83 ሕገ ወጥ የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ላይ እስራት አሊያም የገንዘብ ቅጣት በየነ

የታንዛኒያ ካርታ

የኢትዮጵያዉያኑ ጉዳይ ፍርድ ቤት የቀረበዉ ባለፈዉ ዓርብ ሲሆን የኢሪንጋ ፍርድ ዉሳኔም ያልጠበቁት መሆኑን በእምቤያ ግዛት የኢንተርኔት ጋዜጠኛ ወይም ጦማሪ የሆነዉ ፍራይደይ ሲምባያ ለቪኦኤ ገልጿል።

የታንዛንያ ፍርድ ቤት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሃገሬ ገብተዋል ያላቸዉ በ83 ኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ላይ በእያንዳንዳቸዉን 3 ዓመት እስራት ወይም ወይም በአንድ ሚሊዮን ተኩል የታንዛንያ ሺሊንግ (የአስር ሺህ የኢትዮጵያ ብር) ቅጣት በየነ።

የኢትዮጵያዉያኑ ጉዳይ ፍርድ ቤት የቀረበዉ ባለፈዉ ዓርብ ሲሆን የኢሪንጋ ፍርድ ዉሳኔም ያልጠበቁት መሆኑን በእምቤያ ግዛት የኢንተርኔት ጋዜጠኛ ወይም ጦማሪ የሆነዉ ፍራይደይ ሲምባያ ለቪኦኤ ገልጿል።

ፍለሰተኞቹን ሲያጓጉ የተያዙ ሁለት የታንዛንያ ዜጎችም እያንዳንዳቸዉ በ5 ዓመት እሥራት ወይም አንድ ሚሊዮን ተኩል የታንዛንያ ሺሊንግ እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ በይኖአል።

የአሜርካ ድምጽ ዉሳኔ የተላለፈባቸዉን የኢትዮጵያ ዜጎችን ጉዳይ በማስመልከት ናይሮቢ በኬንያ የሚገኘዉን የኢትዮጵያን ኤምባሲ ለማነጋገር ያረገዉ ሙከራ አልተሳካም።

የድምጽ ፋይሉን በመጫን ገልሞ ዳዊት ከናይሮቢ የላከዉን ዝርዝር ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የታንዛኒያ ፍርድ ቤት 83 ሕገ ወጥ የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ላይ እስራት አሊያም የገንዘብ ቅጣት በየነ