በሰሜን ሦሪያ ክፍል በተቆጣጠሩት ግዛት ላይ የራስ ገዝ ፌደራል ክልል እንሚያውጁ የግዙፉ የሶሪያ ኩርድ ፓርቲ አባላት አስታወቁ።
ሶሪያ ውስጥ የሚገኙት እነዚሁ ኩርድ መሪዎች አክለውም አረቦችንና ቱርክሜኖችን ጨምሮ ሌሎችም የጎሣና የሃይማኖት ቡድኖች በክልሉ አስተዳደር ውስጥ ውክልና እንደሚኖራቸው ገልፀዋል።
የኩርድ የፖለቲካ መሪዎቹ ይህንን የራስገዝ ፌደራል ክልል የመመሥረት ሃሣባቸውን ያሳወቁት ተዋጊዎቻቸው ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር ውጊያ ገጥመው በቀጠሉበት ወቅት ነው።
ሰሜን ሶሪያ ውስጥ ፌደራል መንግሥቱን ይፋ የማድረጉ ዝግጅት በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የኩርድ የውጭ ጉዳዮች ከፍተኛ ተጠሪ የሆኑት ኢድሪስ ናሳን በኩርዶቹ ከተያዘችው ኮባኒ ከተማ ለአል ጃዚራ ቴሌቪዥን ገልፀዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶሪያ አምባሣደር ባሻር አል ጃፋሪ
ጄኔቫ ላይ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ግን “በሦሪያዊያን መካከል ክፍፍልን መዝራት የሚሠራ አይደለም” ብለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ባለው የአሌፖ ከተማ ክፍል የሚኖሩት ካቶሊክ ጳጳስ አቡነ አንቷን አውዶ በውጭ ኃይሎች የሚጫን የፖለቲካ መፍትኄ እርባና እንደማይኖረው ጠቁመው ሦሪያዊያን እራሳቸው ተሰባስበው ለአምስት ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም እንዲመክሩ አሳስበዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5