በኦሮሚያ ተቃውሞዎች የማሕበረሰብ ድረ-ገጽ ሚና

  • ሔኖክ ሰማእግዜር
የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃንም በዚያን ቀን #OromoProtests በሚል በብዛት በፌስቡክና በትዊተር መልእክቶች፣ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በስፋት መሰራጨት ጀመሩ።

በህዳር ወር የመጀመሪያ ሳምንት፤ በኦሮሚያ ጊንጪ ከተማ አካባቢ የሚገኝ ደን ለአንድ የግል ኢንቨስተር “ተሽጦ መቃጠል ጀመረ፤ የአንድ ትምህርት ቤት እግር ኳስ መጫወቻ ሜዳም እንዲሁ ለልማት” በሚል ተሰጠ ሲሉ የከተማዋ ወጣቶች ወደ አደባባይ ወጡ።

የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃንም በዚያን ቀን #OromoProtests በሚል በብዛት በፌስቡክና በትዊተር መልእክቶች፣ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በስፋት መሰራጨት ጀመሩ።

በማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን ከሚሰራጩት መልእክቶች፤ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች መካከል የሚበዙት ከዩናይትድ ስቴይትስና ከአውሮፓ የወጡ ናቸው፤ የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን እንቅስቃሴን የሚከታተለው “Keyhole Hashtag Tracking” መረጃ መሰረት።

41 ከመቶ ከዩናይትድ ስቴይትስ፤ 9ከመቶ ከካናዳ፤ ከአውሮፓ ደግሞ ወደ 25 ከመቶ የሚጠጋ፤ ሲሆን ከኢትዮጵያ ደግሞ 17 ከመቶ መረጃዎች መጥተዋል።

ጌታቸው ጉተማ ከሚኖርበት ካናዳ በፌስቡክ ቀኑን ሙሉ መረጃ ሲቀበልና ሲያሰራጭ ይውላል። ምንጩ ኦሮሚያና በውጭ የሚኖሩ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅቾና ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም ናቸው፤ የጋቢና የስቱዲዮ እንግዳ ነው። ትግዕስት ገሜ በቪኦኤ አፋን ኦሮሞ አገልግሎት የድረ-ገጽ አዘጋጅ ናት። ከሔኖክ ሰማእግዜር ጋር ያደረጉት ውይይት ቀጥሎ ይቀርባል።

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ተቃውሞዎች የማሕበረሰብ ድረ-ገጽ ሚና - ፎስ ቡክ ታውን ሆል