“ኢቦላን እንዴት መቆጣጠር እንዳለን እናውቃለን። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ከምዕራብ አፍሪቃ አገሮች ጋር በመሥራት ለሥኬት የበቃ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል። ይህ ባይሆን ዓለም አቀፍ ቀውስ ይሆን ይችል ነበር። ዚካን በተመለከተ ግን ሳይንቲስቶች ክትባት ለማግኘት ተግተው እየሰሩ ነው። እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ ጊዜ ሊጠይቅ ይችላል።” ዶ/ር ቶማስ ፍሪዳን የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዲሬክተር።
አዲስ አበባ —
ለዚካ ቫይረስ የሚሰጥ ክትባት ለማግኘት እስከ ሁለት ዓመት ሊወስድ እንደሚችል የገለጡት የUS የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል CDC ዲሬክተር፤ የባለ ሞያዎች ጥረት ግን መቀጠሉን አስረድተዋል።
ዲሬክተሩ ዶ/ር ቶማስ ፍሪዳን አዲስ አበባ ላይ በመካሄድ ላይ ባለውና በክትባቶች ላይ ባተኮረው የአፍሪቃ የጤና ሚንስትሮች ጉባኤ ላይ ተገኝተዋል።
Your browser doesn’t support HTML5
በክትባቶች ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ አበባ ላይ እየተካሄደ ነው