በወቅቱ የፍልሰተኞች ቀውስ የአውሮፓ ሕብረት ለፈጸመው ስህተት መቄዶንያ $28 ሚልዮን እንድትከፍል ተገዳለች ሲሉ ፕሬዚደንቷ ተናገሩ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በወቅቱ የፍልሰተኞች ቀውስ የአውሮፓ ሕብረት ለፈጸመው ስህተት መቄዶንያ $28 ሚልዮን እንድትከፍል ተገዳለች ሲሉ ፕሬዚደንቷ ተናገሩ።
ፕሬዚደንት ጆርጅ ኢቫኖቭ ከጀርመኑ ጋዜታ ቢልድ (Bild) ጋር ባካሄዱት ቃለ-ምልልስ፣ በፍልሰተኞች መበራከት የተነሳ አገራቸው ከፍተኛ ችግርስ ውስጥ እንደገባች አመልክተው ይህም መቄዶንያ ውስጥ ብሔራዊ ቀውስ እስከማወጅ መደረሱን ተናረዋል።
ፕሬዚደንቱ አክለውም፣ መቄዶንያ ከፍልሰተኞች ላይ ወደ 9,000 ያህል የተጭበረበሩ ወይም የተሰረቁ ፓስፖርቶችን እንደያዘች ጠቅሰው፣ ጀርመን ልታጋራን የሚገባውን መንፈጓም አንዱ የኪሳራችን ሚክናት ነው ብለዋል።