በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶሪያ ስደተኛ እንዳይመጣብን ማለት የሚጠቅመው አይሲስን ነው ሲሉ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ አስገነዘቡ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ኣሜርካ ለስደተኞችን በሯ ክፍት ነው ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ሶሪያውያን ስደተኞችን ወደአሜሪካ አምጥቶ ማስፈርን የሚቃወሙትን ፖለቲከኞች ነቀፉ። ይህን አስተሳሰብ አሸባሪዎች ተዋጊ ለመመልመል ሊጠቀሙበት ይችላሉ ሲሉ ፕሬዚደንቱ አስረድተዋል። የቪኦኤ የዋይት ሃውስ ዘጋቢ ሜሪ አሊስ ሳሊናስ (Mary Alice Salinas) ፕሬዚደንቱ ከእስያ ፓሲፊክ ሃገሮች መሪዎች ጉባኤ ላይ ካሉበት ከፊሊፒንስ ዋና ከተማ ማኒላ ያጠናቀረቸውን ዘገባ ቆንጂት ታዬ ታቀርባለች።

ባለፈው ዓርብ ፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ውስጥ የደረሱትን የሽብር ጥቃቶች ተከትሎ ኣንዳንድ ሪፑብሊካን ፖለቲከኞች የ ዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሶሪያውያን ስደተኞችን የማስፈር መርሃ ግብሩን ይሠርዝ ወይም ደግሞ ክርስቲያን ስደተኞችን ብቻ እናምጣ የሚል ጥሪ ማሰማት ጀምረዋል። ይህ መሆን ያለበት አገራችን አሸባሪ እንዳይገባብን ለመከላከል ነው በማለት ይሙዋገታሉ።

ፕሬዚደንት ኦባማ ይህን ኣስተሳሰብ እንዲህ ሲሉ አውግዘውታል “ አንድ የሽብር ጥቃት ሲደርስ ምላሻችን በፍርሃት መዋጥና መረበሽ ከሆነ አይበጀንም።”

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አስር ሺህ ሶሪያውያን ስደተኞችን ተቀብሎ ለማስፈር ያለው ዕቅድ እንደጫረው ክርክር ሁሉ አውሮፓ ውስጥም ስደተኛን ማስገባት የደህንነት ኣደጋ ሊያስከትል ይችላል? የሚለው ስጋት እያነጋገረ ነው።

ከወዲሁ ከሃያ ኣራት ኣራት በላይ የአሜሪካ አገረ ገዢዎች ሶሪያውያን ስደተኞች ክፍለ ሀገራችው እንዳይሰፍሩ ለመከልከል ዕቅድ እንዳላቸው እየተናገሩ ናቸው። ይህ ኣሉ ፕሬዚደንት ኦባማ አሜሪካ የምትመራባቸውን እሴቶች የሚቃረን የዕስልምና መንግስት ነኝ የሚለውን ቡድን ተዋጊዎች የሚረዳ ነው።

“እስልምና እና ምዕራቡ ዓለም ጦርነት ላይ ናቸው የሚለውን ኣስተሳሰብ አይሲል ይጠቀምበታል። ስለዚህም ሃላፊነት በሚያሻው ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች በጦርነት ከሚታመስ ሃገር ለክርስቲያኖች ከሙስሊሞች የተሻለ ጥበቃ መሰጠት አለበት የሚል ነገር መናገር የሚያገለግለው ኣይሲልን ነው” ሲሉ ፕሬዚደንት ኦባማ አስረድተዋል።

ይልቁንስ አሉ ፕሬዚደንቱ የዩናይትድ ስቴትትስ ምክር ቤት አባላት ሶሪያ ውስጥ የእስልምና መንግስትን በወታደራዊ ሃይል ለመውጋት የሚፈቅድ ህግ ቢያቀርቡ ይሻላል። ዘገባውን ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የሶሪያ ስደተኛ እንዳይመጣብን ማለት የሚጠቅመው አይሲስን ነው ሲሉ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ አስገነዘቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:27 0:00

XS
SM
MD
LG