በሥራና በሃላፊነት ቦታዎች ተመጣጣኝ የጾታ ዉክልና እንዲኖር ለማድረግ የሚወጡ ሕጎች ብቻቸዉን ዉጤት ማምጣት አይችሉም ሲሉ የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር ዲላሚኒ ዙማ ተናገሩ።
አዲስ አበባ —
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ በአፍሪቃ ሕብረት በተከበረበት ስነስርዓት ላይ የተናገሩትሊቀመንበር ዲላሚኒ ዙማ እኩል ዉክልና ይኖር ዘንድ ሕጎቹ በሚገባ ስራ ላይ የሚዉሉበት መንገድሊኖር ይገባል ብለዋል።
ከዚሁ ከጾታ እኩልነት አንጻር ሲታይ በኢትዮጵያ የተገኘዉን ዉጤት ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮያብራሩት በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ዳይሬድተር ጄኔራል አምባሳደርዶክተር ደስታ ወልደዩሐንስ በ1987 ዓም 13 የነበረዉ የሴት ፓርላማ አባላት ቁጥር አሁን ወደ 200 ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።
የድምጽ ፋይሉን በመጫን ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬዉ ዘገባ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5