በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስተባባሪነት በሶርያ መንግስትና በአማጽያን መካከል በጄኔቫ የሚካሄደው የሰላም ንግግርም ቀጥሏል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ከሩስያው ፕረዚዳንት ቭላዲሚክር ፑቲን ጋር ለመነጋገር በመጪው ሳምንት ወደ ሞስኮ ያመራሉ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ሀይሉን ከሶርያ ማስወጣቱን በመቀጠል ተጨማሪ አውሮፕላኖች እንዳስወጣ ዛሬ አስታውቋል።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስተባባሪነት በሶርያ መንግስትና በአማጽያን መካከል በጄኔቫ የሚካሄደው የሰላም ንግግርም ቀጥሏል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ከሩስያው ፕረዚዳንት ቭላዲሚክር ፑቲን ጋር ለመነጋገር በመጪው ሳምንት ወደ ሞስኮ ያመራሉ።
ሩስያ ወታደሮችዋን ከሶርያ ለማስወታት ስለመወሰንዋና ስለ ሶርያው የሰላም ንግግር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሶርያ ለአምስት አመታት ያህል ሲካሄድ የቆየው የእርስ-በርስ ጦርነት ፖለቲካዊ መፍትሄ ሊያገኝ ስለሚልበት መንገድ ለመነጋገር ከፕረዚዳንት ፑቲንና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርገይ ላቭሮቭ ጋር እንደሚገናኙ ጆን ኬሪ ገልጸዋል።
ሶርያ ውስጥ በመንግሥትና በአማጽያኑ መካከል የተደፈገው ተኩስ የማቆም ስምምነት ለሶስት ሳምንታት ያህል በመዝለቁ በሀገሪቱ የሚካሄደው ውጊያ ጉልህ በሆነ መንገድ ቀንሷል። ኬሪ ግን የሶርያው ፕረዚዳንት ባሽር ዐል ዐሳድ በስልጣን ላይ ከቆዩ ዘላቂ ሰላም ሊኖር አይችልም ይላሉ።