የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ኬንያዉያንን ከጽንፈኞች ጥቃት ለመከላከል ተጨመሪ የፓሊስ ሃይል ያስፈልጋል አሉ።
ናይሮቢ —
የኬንያ ፕረዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ 10,000 ተጨማሪ የፖሊስ ኃይል ምልመላ እንዲደረግ ዉሳኔ አሳለፉ።
ፕረዝደንቱ ይህንን የተናገሩት በትላንትናዉ ዕለት ከ1900 በላይ የሚሆኑ አዲስ የፖሊስ አባላትን በኤምባካሲ ባስመረቁበት ወቅት ነዉ።
ኬንያ አብዛኛዉን ጊዜ በተለይም በአሸባሪዉ ቡድን አልሻባብ ጥቃት የሚሰነዘርባት መሆኑን አስታዉሰዉ ፕሬዚደንቱ ዜጎችን ከጽንፈኞች እና ከተለያዩ ወንጀለኞች ለመጠበቅ የሃገሪቱን የፖሊስኃይል ቁጥር ከፍ ለማድረግ የመንግሥታቸዉ ዓላማ መሆኑንንም ይፋ አድርገዋል።
ገልሞ ዳዊት ከናይሮኒ የላከውን ዘገባ፣ ከዚህ በታች ያለውን ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5