በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ የተገደሉት ኬንያውያን ወታደሮች በሃገራቸው ባንዲራ ተሸፍነው ኬንያ ገብተዋል


በሶማልያ የተገደሉት ወታደሮች አስከሬን ትናንት ሰኞ ማታ ናይሮቢ ሲገባ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ተገኝተው እየተቀበሉ የተነሳ ፎቶ (አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)
በሶማልያ የተገደሉት ወታደሮች አስከሬን ትናንት ሰኞ ማታ ናይሮቢ ሲገባ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ተገኝተው እየተቀበሉ የተነሳ ፎቶ (አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)

ጥቃቱን ያደረሰው አል-ሸባብ “ከባድ ዋጋ ይከፍልበታል”- የኬያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ

ሶማሊያ ውስጥ የተገደሉትን ኬንያውያን ወታደሮች አስከሬኖች በሃገራቸው ባንዲራ ተሸፍነው ኬንያ ገብተዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በሶማሊያ ጌዶ ክፍለ ሃገር ኤል አዴ ከተማ ጥቃቱን ያደረሰው አል-ሸባብ “ ከባድ ዋጋ ይከፍልበታል” ሲሉ ዝተዋል።

ፕሬዚደንት ኬንያታ ዛሬ ለመላ ሃገሪቱ ባሰሙት ንግግር ኬንያ አትንበረከክም ብለዋል።

“አሁን ይህን ንግግር በማደርግበት ሰዓት መከላከያ ሓይሎቻችን የወደቁብንን እና የቆሰሉብንን ጀግኖቻችንን ለሃገራቸው ለማብቃት ከባድ አሰሳና ፈልጎ ማዳን እንቅስቃሴ እያካሄዱ ናቸው። ያ ቅድሚያ ትኩረታችን ነው። ሲሉ ፕሬዚደንቱ አክለዋል።

ኬንያ ለሶማሊያ መረጋጋት መስራቷን ትቀጥላለች በማለት በድጋሚ ያረጋገጡት ኬንያታ ጦርነቱን አል-ሸባብ ጋር እንወስደዋለን ሲሉ ዝተዋል።

ከዓርብ ዕለቱ የአል-ሸባብ ጥቃት በኋላ የደረሰበት የጠፋ አንድ የኬኒያ ሙስሊም ወታደር ቤተሰብ ከባድ ጭንቀት ላይ መሆኑን ገልጿል ። የሃያ ሶስት ዓመቱ ወታደር ኢሳ አብዲ አባት የልጃቸው የእጅ ስልክ ላይ ቢደውሉ መልስ ማጣታቸውንና ከባድ ስጋት ላይ እንዳሉ ለቪኦኤ ገልጸው ከመንግስትም በኩል ተጨበጭ መረጃ እንዳላገኙ አመልክተዋል።

ከተገደሉት ወታደሮች መካከል የአራቱ አስከሬን ትናንት ሰኞ ማታ ናይሮቢ ሲገባ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ተገኝተው ተቀብለዋል።

ጥቃቱ የድረሰበትን የኤል እዴን ካምፕ የኬንያ ወታደሮች ከአል-ሸባብ በኩል ምንም ውጊያ ሳይገጥማቸው መልሰው ተቆጣጥረዋል። አል-ሸባቦቹ ሹልክ ብለው ጫካ እንደገቡ ስነገር ከተማዋ የቀሩት ጥቂት ነዋሪዎች የብቀል ጥቃት በሚል ፍርሃት ላይ እንዳሉ ዘገባው ኣውስቱዋል።

አንዳንድ ኬንያውያን ሃገራችን መከላከያ ሃይሎችዋን ከሶማሊያ ታውጣ በማለት የጠየቁ ሲሆን ፕሬዚደንት ኬንያታ በበኩላቸው "ይህን የሰው ዘር ጠላት ለመውጋት በአንድነት መቆም አለብን" ሲሉ ተማጽነዋል። የዜና ዘገባውን ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ሶማሊያ የተገደሉት ኬንያውያን ወታደሮች አስከሬኖች በሀገራቸው ባንዲራ ተሸፍነው ኬንያ ገብተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:23 0:00

XS
SM
MD
LG