ምዕራባውያን ታጋቾችን አንገት በመቅላት የሚታወቀው ጂሃዲ ጆን በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው አረመኔ ሽብርተኛ መሞቱን የእስልምና መንግሥት ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን አመነ።
ከሳይት ኢንተል ግሩፕ (SITE Intel Group)የተባለው የስለላ መረጃ ክትትል ዌብሳይት እንዳለው ሽብርተኛው ቡድን በእንግሊዝኛ መጽሄቱ ላይ የነፍሰ ገዳዩን መታሰቢያ አውጥቱዋል።
ባለፈው ህዳር ወር የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ ጂሃዲ ጆን ሶሪያ ውስጥ በተካሄደ የድሮን ጥቃት መገደሉን "በርግጠኝነት ለመናገር የሚያበቃ ምክንያት አለን" ማለቱ ይታወሳል።
እውነተኛ ስሙ ሞሃመድ ኤምዋዚ የሆነው ጂሃዲ ጃን የአረብ ዝርያ የእንግሊዝ ዜጋ ሲሆን ፊቱን በጥቁር ጭምብል ሸፍኖ ምዕራባውያንን እያወገዘ የታጋቾችን አንገት ሲቀላ በቪዲዮ የሚታየው ነው። አሜሪካውያን ጋዜጠኞንና እንግሊዛውያን የርዳታ ሰራተኞችን ጭምር ከዚህ በፊት አርዷል። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።
Your browser doesn’t support HTML5
ጂሃዲ ጆን በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው ሽብርተኛ መሞቱን የእስልምና መንግሥት ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን አመነ