ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምሕርት ክፍል የቀድሞ መምሕር ነበሩ። በተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት የሰብዓዊ መብትና መልካም አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ኾነው ሠርተዋል።በማኅበራዊ ሚዲያ በተለይም ፌስቡክ ላይ በኦሮሚያ የተነሳውን ተቃውሞ በትኩረት እየተከታተሉ አስተያየታቸውን በማስፈር ይታወቃሉ፡፡ ጽዮን ግርማ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ አነጋግራቸዋለች፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ —
ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ በድጋሚ ያገረሸውና አራተኛ ወሩን የያዘው በኦሮሚያ ክልል በስፋት እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ሲኾን አሁን ይህ ተቃውሞ ተባብሶ የብዙ ሰው ሕይወት አሳጥቷል ፣በርካቶች ቆስለዋል እንዲሁም ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ታሥረዋል፡፡
"የማስተር ፕላኑ እቅድ ይሰረዝ" የሚለው ጥያቄም፣ ስለተገደሉት ሰዎች ካሳና ፍትሕ ይሰጥ፣የታሠሩ ይፈቱ፣መብቶቻችን ይከበሩ እንዲሁም መንግስት የፀጥታ ሃይሉን ሰብስቦ መመለስ ይኖርበታል የሚሉ ጥያቄዎችን ይዞ መጥቷል፡፡
በመንግሥት በኩልም ሰልፈኞቹ ከኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ጋራ ምንም ግንኙነት የሌለላቸው፣ የታጠቁ እና የተደራጁ ቡድኖች ናቸው ሲል ይከሳል፡፡ሠራዊቱ ይውጣ የሚለውን በተመለከተም አስተያየት የሰጡት የኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ ጌራቸው ረዳ ”ሠራዊቱ ከሰፈረበት የት ይሄዳ?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ እና መንግሥት የሰጠውን ምላሽ በተመለከተ ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ከጽዮን ግርማ ጋር ቆይታ አደርገዋል፡፡
ሙሉ ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5