በትግራይ ጉዳይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔና የባለሞያ አስተያየት

  • እስክንድር ፍሬው

ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ

የኢትዮጵያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ፌዴራሉ መንግሥት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ወስኗል።

ውሳኔው ምክር ቤቱ ባለፈው ነሃሴ አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባኤ በትግራይ ክልል የተካሄደው ምርጫ እንዳልተደረገ፣ እንዳልተፈፀመና እንደማይፀና የደረሰበት ድምዳሜ ተከታይ መሆኑን ተገልጿል። ይህ ውሳኔ የበጀት ጉዳዮችንም እንደሚያካትት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ ተናግረዋል።

የፌደራል መንግሥቱ የትግራይን ሕዝብ የልማትና መሰረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎቶች ማዕከል በማድረግ የከተማና የቀበሌ አስተዳደሮችን ጨምሮ ክልሉ ከሚገኙ ህጋዊ ተቋማት ጋር ብቻ የሥራ ግንኙነት እንደሚያደርግም አመልክተዋል አፈ ጉባኤው።

የዚህ ዝርዝር አፈፃፀም በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚወሰንም ጨምረው ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ጉዳይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔና የባለሞያ አስተያየት