በአሁኑ ወቅት የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ዩናይትድ ስቴይትስ በጋራ በዘጠኝ ከሰሃራ ግርጌ የሚገኙ የአፍሪካ ሀገሮች ላይ የተመጠኑና በባለስልጣናት ላይ የተነጣጠሩ ማእቀቦች ጥለዋል።
ከሰሃራ ግርጌ የሚገኙ ሀገሮች መካከል ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ኮት ዲቩዋር፣ ዚምባብዌና በቅርቡ ደግሞ ቡሩንዲ የተለያዩ ምጥን ማእቀቦች ተጥሎባቸዋል።
በሴኔቱ የውጭ ግንኙነት ኮሚቲ የአፍሪካና ዓለም አቀፍ ጤና ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ጄፍ ፍሌክ የመሩት የምስክር አድማጭ ሸንጎ ጉባዔ ረቡእለት ተካሂዷል።
“በነዚህ ሀገሮች የሚገኙ ግለሰቦች ላይ የተነጣጠሩ የተናጠል ማእቀቦች ናቸው። በሚበዙት ሀገሮች ደግሞ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማእቀብ አስቀምጠናል። እነዚህ ከገንዘብ ዝውውር ማእቀብ ጋር ተዳምረው ለነዚህ የአፍሪካ ሀገሮች ፈተና እንደሚሆኑ ይታመናል” ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት በተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮችና መሪዎች ላይ የጦር መሳሪያ፣ የጉዞ፣ የገንዘብ፣ የወጭ ገበያ፣ የንግድና ሌሎች ማእቀቦችን ለተለያዩ ግቦችና መርሆዎች ሲባል ሲጥሉ ቆይተዋል።
ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በጦርነት ስትታመስ በቆየችው ሶማሊያ ባለስልጣናትና መንግስት እንዲሁም በኤርትራ ላይ የጦር መሳሪያ፣ የገንዘብና የጉዞ ማእቀቦች ተጥለዋል።
በነዚህ ሀገሮች የሚገኙ ግለሰቦች ላይ የተነጣጠሩ የተናጠል ማእቀቦች ናቸው። በሚበዙት ሀገሮች ደግሞ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማእቀብ አስቀምጠናል። እነዚህ ከገንዘብ ዝውውር ማእቀብ ጋር ተዳምረው ለነዚህ የአፍሪካ ሀገሮች ፈተና እንደሚሆኑ ይታመናል።በዩናትድ ስቴትስ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቲ የአፍሪካና ዓለም አቀፍ ጤና ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ጄፍ ፍሌክ
ከሁለት ሳምንታት በፊት የዩናይትድ ስቴይትስ ሴናተር ኤድ ማርኪ በዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ካቢላ አስተዳድርና ባለስልጣናት ላይ ማእቀብ እንዲጣል የሚጠይቅ የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ ቀርቧል።
“በዚያች ሀገር ፕሬዝደንት ጆሴፍ ካቢላ በስልጣን ለመቆየት ሲሉ የማይቧጥጡት ስልታዊ ምክንያት የለም። የተቋማትን ገለልተኝነት ከማሳጣት ጀምሮ፣ የፖለቲካ ተቃዋሚዎቻቸውን ማዋከብና የምርጫውን ቀን በማራዘም በህግ ከተፈቀደላቸው ገደብ አልፈው በስልጣን ለመቆየት ሲጥሩ እናያለን።” ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአፍሪካ ላይ ከሌሎች አህጉሮች በሚበዛ ቁጥር የተለያዩ ማእቀቦችን ሲጥል ቆይቷል፤ ጥሎ ይገኛል በማለት በዝርዝር የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡት አስቀድመው በሁለት የአፍሪካ ሀገሮች የዩናይትድ ስቴይትስ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ፕሪንስተን ላይም ናቸው።
ማእቀቦቹ ግጭቶችን ለማብረድና በተለይ በቅርብ ጊዚያት ደግሞ የእርስ በርስ ግጭቶችን ጉዳት ለመቀነስ የታሰቡ ናቸው። በእርግጥ ከነዚህ መካከል በሁለት ሀገሮች መካከል የተፈጠሩ ግጭቶች ያስከተሏቸው ማእቀቦችም ነበሩበት። ኢትዮጵያና ኤርትራ ባካሄዱት የሁለት ዓመታት የድንበር ግጭትና በኤርትራና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረ ግጭትን ተንተርሶ የጦር መሳሪያ ማእቀቦች ተላልፈው ነበር።
“በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በጣም ጥንቃቄ የሚያስፈልገውና አደገኛ ገጽታ ሊኖረው የሚችል ሁኔታን እንመለከታለን። የስልጣን ዘመንን የማራዘም ጉዳይ ለአንድ ወይንም ከዚያ በላይ የስልጣን ጊዜ የመቆየት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ ሁከትና ብጥብጥ የሚያስነሳ ከሆነ የሰላምና መረጋጋት ጉዳይ ይሆናል። በጎንጎ ጉዳይ የሚያሰጋኝ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስምምነትና መግባባት ላይ አለመድረሱ ነው።”
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለያዩ ሀገሮች አስተዳድርና መሪዎች ላይ የሚጥለው ማእቀብ የተመጠነ እንዲሆን በተለይ የዩናይትድ ስቴይስም መንግስት በጥቅል ህዝቦችንና የሀገሮችን ምጣኔ የሚጎዱ ማእከቦችን የምስክር ቃል የሰጡት ባለሙያዎች መክረዋል። የፖሊሲ አውጭዎችም በተለይ በአፍሪካ ሀገሮች ላይ የሚተላልፉ ማእቀቦች ውጤቶቻቸው እየታዩና እየተገመገሙ እንዲሄዱ መደረጉ አስፈላጊ እንደሆነ የተረዱት ጉዳይ እንደሆነ የህዝብ ተወካዮቹ ገልጸዋል።
Your browser doesn’t support HTML5