በራስ-ገዟ ሶማሌ-ላንድ የሚገኙ ባለሥልጣናት በሰጡት መግለጫ፣ ወደ ባሕረ-ሰላጤው ያመሩ የነበሩ 80 ኢትዮጵያውያን ህገ-ወጥ ስደተኞች፣ ሰሜናዊ ሶማልያ ውስጥ ትናንት ማታ መያዛቸውን አስታወቁ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በራስ-ገዟ ሶማሌ-ላንድ የሚገኙ ባለሥልጣናት በሰጡት መግለጫ፣ ወደ ባሕረ-ሰላጤው ያመሩ የነበሩ 80 ኢትዮጵያውያን ህገ-ወጥ ስደተኞች፣ ሰሜናዊ ሶማልያ ውስጥ ትናንት ማታ መያዛቸውን አስታወቁ።
የሶማሌ-ላንዷ ሳናግ(Sanaag) ገዢ አህመድ አብዲ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፣ የሶማሌ-ላንድ የባሕር ኃይል አባሎች፣ ከጉዞው ድካም ጋር በተያያ በረሀብና በውኃ ጥን የሞቱ የሰባት ሰዎች አስከሬን ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ሌሎች ሦስት ኢትዮጵያውያን ደግሞ ወደ የብስ ሲወጡ ሞተው መገኘታቸውንም አመልክተዋል።
ገዥው እንደገለጹት ጀልባዋ የተነሳችው ፑንትላንድ ከምትገኘው ቦሳሶ ነው።
ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ኢትዮጵያውያን የተመቻቸ ኑሮና ዋስትና ፍለጋ በሰሜናዊ ሶኢማልያ ወደብ በኩል ከሃገር ለመውጣት ይጠቀማሉ።
የዜና ዘገባ አለን ከዚህ በታች ካለው ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5