የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ጉባዔ በዛሬው ዕለት በቱርክ ኢስታንቡል ተከፍቷል። የረድኤት ተቋማት መሪዎችና መንግሥታት በተወከሉበት በኢስታንቡሉ ጉባዔ የተገኙት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ በተሰጠው ምላሽ የተሻሉ የተባሉትን አሠራሮች በተመለከተ ለመድረኩ አቅርበዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ለሁለት ቀናት የሚዘልቀው የዚህ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጠራው ጉባዔ አቢይ ዓላማዎች አንዱ በመንግስታቱ ድርጅት ተቋም ውስጥ የሰብዓዊ እርዳታ አሰጣጥ መዋቅሮችን ለመፈተሽና ለማሻሻል ነው።
#Ethiopia Showcases Best Practices in Drought Response at #WHSummit Side Event https://t.co/LGz9vTFfJ1 pic.twitter.com/xg4sA4YS9f
— UNICEF Ethiopia (@UNICEFEthiopia) May 23, 2016
የረድኤት ተቋማት መሪዎችና መንግሥታት በተወከሉበት በኢስታንቡሉ ጉባዔ የተገኙት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ በተሰጠው ምላሽ የተሻሉ የተባሉትን አሠራሮች በተመለከተ ለመድረኩ አቅርበዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበርያ የኢትዮጵያው ጽ/ቤት ወይም ኦቻ የእቅድና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ኃላፊ ቾይስ ኦኮሮ ማምሻውን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስለ ጉባኤው አስረድተዋል። ሳሌም ሰለሞን ኢትዮጵያን ለመታው ድርቅ በአሁኑ ወቅት እየተሰጠ ስላለው ምላሽና ጥረቶች አነጋግራቸዋለች። ዝርዝሩን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።
Your browser doesn’t support HTML5