በቅርቡ ሁለት ጊዜ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ተቃዋሚዎች ተራቸውን ድል ሊያስመዘግቡ ተስፋ ሰንቀው ተነስተዋል።
ከተቃዋሚው ወገን ስካሁን ለፕሬዚደንትነት ለመወዳደር በዕጩነት የቀረቡት ተቃዋሚ መሪ ሞኢሲ ካቱምቢ አሜሪካዊያን ቅጥረኞችን አሰማርተዋል ተብለው ክስ ተመስርቶባቸዋል። ክሱን ያስተባብላሉ።
በሌላ በኩል ህገ መግስታዊው ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ካቢላ ለህዳር የታቀድው ምርጫ እንዲዘገይ ከተደረገ ስልጣን ላይ መቆየት ይችላሉ ሲል በይኗል። ያሁኑ የስልጣን ዘመናቸው እ.አ.አ ታህሳስ አስራ ዘጠኝ ቀን ያበቃል።
የፍርድ ቤቱ ውሳኔው ተቃዋሚዎችን እጅግ በጣም አስቆጥቷል። አንደኛው ዋና የተቃዋሚ ጥምረት “ለዲሞክራሲ መቃብር እየማሱ ነው ሲል የገለጸውን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለመቃወም አገር አቀፍ ሰልፍ ጠርቷል። "ተቃዋሚ መሪ ማርቲን ፋዩሉ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል ህገ መንግስታዊው ፍርድ ቤት የካቢላ ንብረት የሆነ አጎብዳጅ ፍርድ ቤት ነው። ውሳኔውን እንደማንቀበል እንሳየዋለን።" ብለዋል።
የበርካታ የኮንጎ ከተሞች አስተዳደሮች ሰልፍ አልፈቀዱም ተቃዋሚዎች ህገ መንግስቱ በሚያዘው መሰረት እኛ የሚጠበቅብን ሰልፍ ለድረግ ማቀዳችንን ለባልስልጣናቱ ማስታውቅ ብቻ ነው በማለት እየተከራከሩ ናቸውና ሰልፎቹ መካሄዳቸው አይቀርም ይሆናል።
ዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ውስጥ ግን አገረ ገዢው ፖሊስ ተቃዋሚዎቹና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ አድርገው መነጋገራቸውን ተከትሎ ሰልፉ በዕቅዱ መሰረት ሊከናወን ይችላል።
ሁከት ሊቀሰቀስ እንደሚችል ግን ስጋት አለ። የኮንጎ የፀጣታ ሃይሎች በተቃውሞ ሰልፎች ላይ ከባድ ርምጃ በመውሰድ የሚታወቁ ሲሆን በቅርቡ ተቃዋሚ ዕጩ የማርቲን ካቱምቢ ደጋፊዎች ስብሰባ በትውልድ ከተማቸው ሉሙምባሺ ተካሂዶ ፖሊሶች ሃይል ተጠቅመው በትነዋል።
ገዢው ፓርቲ ለነገ ሐሙስ የራሱን ዝግጅቶች እያቀደ ነው የሚሉ ዘገባዎች እየተሰሙ በመሆኑ በየጎዳናው ውጥረቱን ይበልጡን ሳያቀጣጥለው እንደማይቀር ይታወቃል።
ዊሊያም ክሎውስ ከኪንሻሳ ዘገባ አስተላልፏል ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታ።
Your browser doesn’t support HTML5