በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ መንግስት ምርጫዎችን የሚያመቻች “ተጨባጭ ርምጃ" እንዲወስድ ዩናይትድ ስቴትስ አሳሰበች


በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሲቪላዊ ጸጥታ፡ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር ሳራ ሲዋል(Sarah Sewall)
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሲቪላዊ ጸጥታ፡ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር ሳራ ሲዋል(Sarah Sewall)

የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፑብሊክ መንግስት በሀገሪቱ ወደፊት ለሚካሄዱ ምርጫዎች ለመዘጋጀት ተጨባጭ ርምጃዎች እንዲወስድ በሀገሪቱ ጉብኝት ላይ ያሉ ኣንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት ኣሳሰቡ። በተጨማሪም የሀገሪቱን ግጭቶች ለመፍታት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልእኮ በሚያደርገው ጥረት መንግስት ሙሉ በሙሉ እንዲተባበር ተማጽነዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሲቪላዊ ጸጥታ፡ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር ሳራ ሲዋል(Sarah Sewall) የኮንጎን ህገ መንግስታዊ ሂደቶች የሚጥሱ በአጸፋው ርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ኣስጠንቅቀዋል። ሳራ ሲዋል ከትናንት ወዲያ ቅዳሜ ምስራቅ ኮንጎ Goma ውስጥ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል። የቪኦኤው Nick Long ተከታትሎታል።

ረዳት ሚኒስትር ሳራ ሲዋል (Sarah Sewall) ኣንድ ሳምንት የፈጀው የኮንጎ ጉብኝታቸው በሁለት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል። አንደኛው ምርጫዎችን የሚመለከት ሲሆን ሁለተኛው የሀገሪቱ ጦር ሰራዊት እና በዚያ ያለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅ ተልእኮ (MONUSCO) ትብብር ጉዳይ ነው።

መራጭ ምዝገባውን እና በምርጫው ወቅት ጸጥታ ጥበቃውን የሚያረግግጡ ርምጃዎችን መውሰድ ኣስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት የኣሜሪካ ዲፕሎማት ምርጫዎቹ በሚካሄዱበት የጊዜ ሰሌዳ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚገባ ኣስረድተዋል። ምርጫን የተመለከቱ ጉዳዮች በውይይት እንዲፈቱም ተማጽነዋል።

እንደኛ እምነት የህገ መንግስቱ መርሆች እንዲከበሩ የስልጣን ሽግግርም በሰላማዊ መንገድ እንዲከናወን ከወገናዊነት ነጻ በሆነ መድረክ መወያየት ያስፈልጋል።
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሲቪላዊ ጸጥታ፡ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር ሳራ ሲዋል(Sarah Sewall)

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካሁን ቀደም መንግስቱ ያደረገላቸውን የውይይት ጥሪ ኣላማው ፕሬዚደንት ጆሴፍ ካቢላ ህገ መንግስቱ ከሚፈቅድላቸው ሁለት የስልጣን ዘመን በላይ እንዲቆዩ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ለማድረግ ነው በማለት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ይልቁን አለም ኣቀፍ ኣካል የሚሸመግለው በምርጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ይከፈትልን ሲሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠይቀዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ የኮንጎን ምርጫ ሂዳት ለመደገፍ ሃያ ኣምስት ሚሊዮን ዶላር መመደቡዋን ክፍተኛዋ ዲፕሎማት ገልጸዋል።

“ዩናይትድ ስቴትስ የምርጫው ሂደት ወደፊት እንዲራመድ በሙሉ ቁርጠኝነት እየሰራች ናት ። በጣም የሚያሳዝነው ተጨማሪ ወጪ እንዳንመድብ የመራጭ ምዝገባውን መጀመር እና ምርጫውን እውን የሚያደርጉ ተጨባጭ ርምጃዎች መውሰድ ያለባቸው ተቁዋማት ሂደቱን ያለማቁዋረጥ እያጉዋተቱት መሆናቸው ነው” ብለዋል።

የዝግጅቱ መጉዋደል ሆን ተብሎ የሚደረግ ነው ብለው እንደሚያምኑ ሳራ ሲዋል (Sarah Sewall) ተናግረዋል።

የፕሬዚደንታዊ ስልጣን ዘመን ገደቦችን ለመጣስ የሚደረጉ ሙከራዎችን በተመለከተ ሲናገሩ በቅርቡ በቡሩንዲና በኮንጎ ብራዛቪል የተፈጠሩት ሁኔታዎች የሚያሳዩት የህዝብን ፍላጎት ኣለመቀበል ምን ያህል ኣለመረጋጋትን ሊፈጥር እንደሚችል ነው ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርዋ ኣክለው ሀገራቸው የኣውሮፓ ህብረት እንዳደረገው ሁሉ ቡሩንዲ ውስጥ ብጥብጥ የሚቀሰቅሱ ወገኖች ላይ በቅርቡ የጉዞ ማእቀብ ልትወስንባቸው እንደምትችል ኣስጠንቅቀዋል።

“ህገ መንግስታዊ ሂደቶችን የሚጥሱ ወገኖች ድርጊታቸው ኣጸፋ ጣጣ የሚያመጣባቸው መሆኑን ለማሳመን ከሚረዱ መንገዱች አንዱ ይህ ነው።”የጸጥታ ጉዳይ በተመለከተ ደግሞ የኮንጎ መንግስትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልእኮ (MONUSCO) በምስራቅ ኮንጎ በታጣቂ ቡድኖች

የሚያካሂዱትን በትብብር ዘመቻ እንዲቀጥሉ ኣሳስበው መምረጥ ግን የመንግስቱ ፋንታ መሆኑን ገልጠዋል።

"ታጣቂዎቹ ቡድኖች እንቅስቃሴአቸውን መቀጠላቸውን ኣስመልክቶ ያለው ዋናው ችግር መንግስቱ ከ(MONUSCO) ጋር በጋራ ርምጃ መውሰድን በሚመለከት የያዘው የፖለቲካ ኣቁዋም ነው” ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስዋ ዲፕሎማት፡ በኮንጎ ጉብኝታቸው ያነጋገሩዋቸውን የኮንጎ ባለስልጣናት አሁንም በእስር ላይ ስለሚገኙት ኣፍቃሪ ዲሞክራሲ መሪዎች ያነሱባቸው መሆኑ ገልጸዋል። መንግስቱ እምነታቸውን በሰላማዊ መንገድ የሚገልጹ ሰዎችን ከማሳደድ እንዲቆጠብና በሰላማዊ መንገድ ሃሳብን መግለጽንና የወንጀል ተግባርን ማደበላለቁን እንዲያቆም ኣሳስቤአለሁ ብለዋል።

ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ መንግስት ምርጫዎችን የሚያመቻች “ተጨባጭ ርምጃ" እንዲወስድ ዩናይትድ ስቴትስ አሳሰበች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:01 0:00

XS
SM
MD
LG