ምስራቃዊ ኮንጎ ሰሜን ኪቩ ክፍለ አገር ከጎማ በስተምእራብ 70 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ከሚገኘዉ የሞኮቶ (Mokoto) ካምፕ ወደ 4 300 የሚሆኑ ስደተኞች እየለቀቁ ናቸዉ ብለዋል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት የኦቻ ቃል አቀባይ Nadia Berger።
ካምፑ ስለተቃጠለ ሰዎቹ ሌላ መጠለያ መፈለግ ግድ ሆኖባቸዋል። በአሁኑ ጊዜ ሕዝቡ ወዴት እንደሄደ ባናዉቅም ሁኔታዉን የሚከታተል መንግስታዊ ድርድት ቡድን ወደ ሞኮቶ ተልኮአል ብለዋል።
የክፍለ አገሩ ባለስልጣናት ለጸጥታ ያሰጋናል በማለት ካምፑን እንደሚዘጉ ከአንድ ሳምንት በፊት ማሳወቃቸዉን በርገር አስታዉሰዉ፣ ኦቻና ሌሎች የተራድኦ ድርጅቶች ካምፑን ከመዘጋት ለማዳን ጥረት አድርገዉ እንደነብ ታዉቋል።
በሰሜን ኪቩ በመንግስትና በተለያዩ የታጠቁ ሃይሎች መካከል በሚካሄድ ፊልሚያ ለዓመታት በአመጽ ስትናወጥ መቆየትዋ ይታወቃል። ከአካባቢዉ ከ 600 መቶ ሽህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዉ እንደሚገኙ ተነግሯል።