ፕሬዚደንት ጆሴፍ ካቢላ በቅርቡ ያወጁትን የሰላም ጥሪ፣ የBDK ንቅናቄ መሪ Ne Muanda Nsemi ደግፈውና ምሕረትም ጠይቀው እንደነበር ታውቋል። በዚሁ መሠረት ነው ፕሬዚደንት ካቢላ፣ ዕድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ ለሆኑ የንቅናቄው እስረኞ ምህረት ያደረጉት።
ቢ ዲ ኬ (BDK) እራሱን እንደ ሃይማኖታዊ ንቅናቄ አድርጎ ነው የሚቆጥረው። ዓላማውም፣ ደቡባዊ ኰንጎ ዴሞክራቲክ ውስጥ ላለችው የባስ ኮንጎ (Bas Congo) ክልል፣ የራስ አስተዳደር እንዱመሰረት ነው። መሪውም ኔ ሟንዳ ንሰሚ (Ne Muanda Nsemi) ወደ ንቅናቄው የገቡት ደግሞ ራዕይ ተገልጦላቸው እንደሆነ ያምናሉ።
እናም ፕሬዚደንት ካቢላ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ባስተላለፉት ብሔራዊ ጥሪ፣ ዛሬ በጀመረው በአዲሱ የ2016 ዓም የፖለቲካ ድርድር ለመጀመር መወሰናቸውን ይፋ አደረጉ።
ሆኖም አንዳንድ ተተቃዋሚዎች፣ የካቢላን የሰላም ጥሪም ሆነ የምህረት ዓዋጅ፣ የመደለያና የሥልጣን ማራዘሚያ አድርገው እንደሚያዩት፣ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።
አዲሱ አበበ ያቀናበረውን ዘገባ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።