የፍትህ ሚኒስትር አሌክስ ታምብዌ ምዋምባ በርካታ የቀድሞ አሜሪካውያን ወታደሮች በካታንጋ ክፍለ-ሀገር የካቱምቢ ጠባቂዎች ሆነው እንየሰሩ መሆናቸውን የሚያሳይ “የሰነድ መረጃ” አለን ብለዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፑብሊክ ሞሴ ካቱምቢ (Moise Katumbi) የተባሉ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ባዕዳን ቅጥረኞችን ተጠቅመዋል በሚለው ወሬ ላይ ምርመራ እንደጀመረች የመንግስት ባለስልጣኖች ትላንት ረቡዕ ተናግረዋል።
የፍትህ ሚኒስትር አሌክስ ታምብዌ ምዋምባ በርካታ የቀድሞ አሜሪካውያን ወታደሮች በካታንጋ ክፍለ-ሀገር የካቱምቢ ጠባቂዎች ሆነው እንየሰሩ መሆናቸውን የሚያሳይ “የሰነድ መረጃ” አለን ብለዋል።
ካታንጋ የተባለችው የነሃስ ማዕዳን ያላት ክፍለ-ሀገር አስተዳዳሪ ሆነው ሰርተው የነበሩት ካቱምቢ ባለፈው መስከረም ወር ከፕረዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ መንግስት ወጥተው ከተቃዋሚዎች ጋር ተቀላቅለዋል።
አንድ ተቃዋሚ ቡድን ካቱምቢ በያዝነው አመት በሚካሄደው ፕረዚዳንታዊ ምርጫ እንዲወዳደሩ የሚጠይቅ የስም ዝርዝር ባለፈው እሁድ አቅርቦ ካቱምቢ ተቀብለውታል።
ተቃዋሚው ፖለቲከኛ ባዕዳን ቅጥረኞችን እየመለመሉ ነው የሚለውን ክስ አስተባብለዋል። እኔን በፖለቲካ ለመጉዳት የታቀደ ክስ ነው ብለዋል።