ዶ/ር መረራ በቀረቡበት በአንደኛው ችሎት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጃዋር መሐመድ እንዲቀርቡ ጥሪ የሚያደረገው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ለችሎት ቀርቧል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተከሳሾች ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በሰላሳ ቀን ውስጥ እንዲቀርቡ ተብሏል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት(መድረክ)ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር፣ የኦሮሞ ፌደላራዊ ኮንግረስ (ኦ.ፌ.ኮ) ሊቀመንበርና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የረጅም ዓመት የፖለቲካ ሳይንስ መምሕር የነበሩት ዶ/ር መረራ ጉዲና በዛሬው ዕለት በሁለት ፍርድ ቤቶች ሁለት ችሎቶች መቅረባቸው ታውቋል።
ጽዮን ግርማ ከጠበቃቸው አንዱን አቶ ወንድሙ ኢብሳን ጠይቃ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
Your browser doesn’t support HTML5