በአይቮሪ ኮስቱ ጥቃት 21 ሰዎች ተገድለው ሌሎችም ቆስለዋል

ባለፈው እሑድ አይቮሪ-ኮስት ዋና ከተማ አቢዣን (Abidjan)ውስጥ የተፈጸመው ግድያ፣ በዚያች አገር የሽብርተኛነት አነስተኛው ጅማሮ ነው ተባለ። በጥቃቱ 21 ሰዎች ተገድለው ሌሎችም ቆስለዋል። መንግሥት፣ ሁለት ወታደሮችና ከአጥቂዎቹ መካከል ደግሞ ስድስቱ መሞታቸውንም አመልክቷል። ከተገደሉት ሲቪሎች መካከል፣ እስካሁን ሁለት ብቻ ናቸው የአይቮሪ-ኮስት ዜጎች አለመሆናቸው የተረጋገጠው።

ከመዲናዪቱ አቢዣን (Abidjan የደረሰን የአሜሪካ ድምጽ ባልደረባችን የኤምክሊ ዮብ (Emilie Iob) ዘገባ እንዳመለከተው በዋና ከተማዋ ዋና መንገዶች ላይ የተለመደው ጥድፊያ፣ ወከባና ሩጫ ቀጥሏል፤ የተረጋጋና ጤነኛ ሁኔታ ግን አይታይም።

የአቢዣን ነዋሪ ዮን ግዌ (Yoan Guei) "እንዲህ በቀላሉ የማይነገር ሳይኮሲስ ማለት የአዕምሮ ቀውስ ውስጥ ገብተናል" ነው ያሉት።

ለጥቃቱ አይኪውአይኤም (AQIM) የተባለው ነውጠኛ ቡድን ኃላፊነት የወሰደ መሆኑን በመግለጽ ለአንድ የዜና አውታር መልዕክት አስተላልፏል። ሂውስ ክዋሜ (Hugues Kouame) የተባሉ የአቢዣን ነዋሪ ይህ ቡድን በምዕራባውያንን ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ላይ ጥቃት እንደሚፈጽም ነው የተናገሩት።

በአይቮሪ ኮስት ግራንድ ባሳም ተብሎ በሚጠራ መዝናኛ ስፍራ

ለብዙዎቹ የአቢዣን ነዋሪዎች፣ የእሑዱ ጥቃት፣ አስደንጋጭ እንጂ ድንገተኛ ወይም ያልታሰበ ዱብ-ዕዳ አልነበረም። የአካባቢው ነዋሪ አዳም ኮኔ (Adama Kone) የአሪቱን ወቅታዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁናቴ ለሚረዳ ሰው፣ አስገራሚና ድንገተኛ አልነበረም ብለዋል።

የትና መቼ እንደሚሆን እንጂ፣ የማይቀር እንደነበር ግን እናውቃለን ነው ያሉት። በዚሁ ምክንያት የከተማዋ ነዋሪ የሆኑት ስቴፋኒ ታኖ (Stephane Tanoh)"ገና ለገና ጥቃት ይኖራል ብዬ የአኗኗር ስልቴን (ስታይሌን) አልቀይርም" ባይ ናቸው። አዲሱ አበበ አጠናቅሮ ያቀረበውን ዘገባ ለማዳመጥ፣ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

Your browser doesn’t support HTML5

በአይቮሪ ኮስቱ ጥቃት 21 ሰዎች ተገድለው ሌሎችም ቆስለዋል