ኤርትራ አራት የጂቡቲ የጦር ምርኮኞችን መፍታቷ አዎንታዊ እርምጃ ነው ሲል የአፍሪቃ ህብረት ገለጸ 

  • ሰሎሞን ክፍሌ

የኤርትራና ካርታ

የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ንኮሳዛና ዲላሚኒ ዙማ ዛሬ ሲናገሩ፥ የእሥረኞቹ መለቀቅ፥ ሁለቱ የአፍሪቃ ቀንድ ሀገሮች በግንኙነቶቻቸው መሻሻል ሂደት፥ ቀጥተኛውን አቅጣጫ የሚያመላክት እርምጃ ነው ብለዋል።

ኤርትራ አራት የጂቡቲ የጦር ምርከኞችን መፍታቷ፥ የሁለቱን ሃገሮች ግንኙነት ለማሻሻል አዎንታዊ እርምጃ ነው ሲል የአፍሪቃ ህብረት ገለጸ።

ራስ ዱሜራ፤ የኤርትራና የጂቡቲ ካርታ

የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ንኮሳዛና ዲላሚኒ ዙማ(Nkosazana Dlamini-Zuma) ዛሬ ሲናገሩ፥ የእሥረኞቹ መለቀቅ፥ ሁለቱ የአፍሪቃ ቀንድ ሀገሮች በግንኙነቶቻቸው መሻሻል ሂደት፥ ቀጥተኛውን አቅጣጫ የሚያመላክት እርምጃ ነው ብለዋል።

ኤርትራና ጂቡቲ እ. አ. አ. በሐምሌ 2010 ዓ.ም. በቀጠር መንግሥት ሸምጋይነት የፈረሙትን የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲያደርጉም ሊቀ መንበሯ አስገንዝበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ የአውሮፓ ህብረትም፥ ኤርትራ የጂቡቲ ጦር ምርከኞችን መልቀቋ፥ ለሁለቱ ሃገሮች እርቀ ሰላም መፈጠር ጠቃሚ እርምጃ ነው ሲል በደስታ መቀበሉን አስታውቋል።

ኤርትራና ጂቡቲ እ. አ. አ. በ 2008 ዓ.ም. ወደ ጦርነት የገቡት በግዛት ይገባኛል ንትርክ ሳቢያ እንደነበር ሲታወስ፥ ከሁለቱም ወገን በርካታ ወታደሮች ሞተዋል።

ባጨቃጫቂዎቹ አካባቢዎች የቀጠር ወታደሮች የተመደቡ ሲሆን የዓለሙ ድርጅትም ንትርኩ በሰላማዊ መንገድ እንዲያበቃ ሲወተውት ቆይቷል።