ግብጽ እአአ በ2013 ዓ. ም. እስላማዊው ፕሬዚደንት ሞሃማድ ሞርሲ በጦር ሰራዊቱ ከስልጣን ከተወገዱ ወዲህ ታጣቂዎችን ስትታገል ቆይታለች።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በግብጽ ሁከታማ በሆነው የሲናይ ልሳነ ምድር ታጣቂዎች በፍተሻ ኬላ ላይ ተኩስ ከፍተው አምስት ፖሊሶች መግደላቸውን የአገር አስተዳደር ሚኒስቴሩ አስታወቀ።
የቦምብ ጥቃት በጊዛ ግብጽ እአአ 2016
የሲናይ ትልቋ ከተማ በሆነችው ኤል አሪሺም ትናንት ረቡዕ ማታ በደረሰው ጥቃት ሶስት ፖሊሶች መቁሰላቸውን ሚኒስቴሩ አመልክቷል። ለጥቃቱ ሃላፊነት የወሰደ ወገን ግን የለም።
ግብጽ እአአ በ2013 ዓ. ም. እስላማዊው ፕሬዚደንት ሞሃማድ ሞርሲ በጦር ሰራዊቱ ከስልጣን ከተወገዱ ወዲህ ታጣቂዎችን ስትታገል ቆይታለች።
ለሚደርሱት ለአብዛኞቹ ጥቃቶች የእስልምና መንግሥት ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን ግብረ አበር የሆነ ታጣቂ ቡድን ሃላፊነት ሲወስድ ቆይቷል። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።
Your browser doesn’t support HTML5
ታጣቂዎች በግብጽ ጥቃት ከፍተው አምስት ፖሊሶች መግደላቸው ታወቀ