በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

Sorry! No content for 25 ዲሴምበር. See content from before

ዓርብ 20 ዲሴምበር 2024

የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በረኅብ ለተጎዱ ሰዎች የርዳታ እህል ወደ ወረዳው እንዲገባ ከመንግሥትና ከፋኖ ታጣቂዎች ጋራ ስምምነት ማድረጋቸውን አስታወቁ።

በስምምነቱ መሰረትም የርዳታ እህሉ እየገባ መኾኑን አንድ የኃይማኖት አባት ተናግረዋል። የሰሜን ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል፣ አካባቢው በፋኖ ታጣቂዎች ስር በመኾኑ ለተከሰተው የምግብ እጥረት መንግሥት በቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻለም ብለዋል።

የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በአደረጉት ጥረትም ከ110 ሺሕ በላይ ለሆኑ ሰዎች ከ16 ሺሕ ኩንታል በላይ የርዳታ እህል ወደ ስፍራው እየተጓጓዘ መኾኑን አስታውቀዋል።

የወረዳው ነዋሪ ያለበትን የምግብና የጤና ችግር ለፋኖ ታጣቂዎችና ለመንግሥት አካላት ለማስረዳት ከተመረጡት 18 ግለሰቦች መካከል “አንዱ ነበርኩ” ያሉት ቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዝናቤ ይርዳው በአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረሰው ስምምነት መድኃኒቶችንና አልሚ ምግቦች ወደ ወረዳው መግባት መቻላቸውን ተናግረዋል።

የእህል ርዳታ ወደ ቡግና ወረዳ መጓጓዝ መጀመሩን ባለሥልጣናት አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:06 0:00

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ሁለት የአይና ቡግና ወረዳ ነዋሪ እናቶች፣ ለሕፃን ልጆቻቸው አልሚ ምግቦችን ከጤና ተቋማት ተቀብለው ወደ ቤታቸው እየሄዱ እንደሆነ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ዛሬ ታኅሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በፌስ ቡክ ገጹ በአወጣው መግለጫ በቡግና ወረዳ የምግብ እጥረት ቀውስ ሰለመኖሩ የወጡ ሪፖርቶችን እየተከታተለ መኾኑን አመልክቷል።

"ሁኔታውን መከታተላችንን እና መገምገማችንን እንቀጥላለን" ያለው መግለጫው ቀውሱ መወገዱን ለማረጋገጥ እንደሚሠራም ጠቅሷል።

ኤምባሲው በመግለጫው ቀውሱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን አላካተተም።

የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመደገፍ ፣ አጋሮቹ በአኹኑ ሰዓት በችግሩ በተጠቁት አብዛኞቹ ስፍራዎች የምግብ እና አልሚ ንጥረ ምግቦች ስርጭትን ያጠናከሩ መሆናቸውንም አክሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ፎቶ ፋይል፦ የድሮ-ኦምዱርማን ሠፈር ነዋሪ ሀጅ አህመድ በኦምዱርማን ጉዳት ከደረሰ በኋላ ጉዳት የደረበትን ቤታቸውን ይመለከታሉ
ፎቶ ፋይል፦ የድሮ-ኦምዱርማን ሠፈር ነዋሪ ሀጅ አህመድ በኦምዱርማን ጉዳት ከደረሰ በኋላ ጉዳት የደረበትን ቤታቸውን ይመለከታሉ

በሱዳን በጦር ሠራዊቱ እና በፈጥኖ ደራሽ ኅይሎች መካከል ለ20 ወራት የዘለቀውን አስከፊ ጦርነት ተከትሎ “እስከዛሬ ከተመዘገቡት ሁሉ ትልቁን ሰብአዊ ቀውስ የተሸከመች ሀገር ሆናለች” ሲል የዓለም ነፍስ አድን ኮሚቴ አመለከተ፡፡

በተቃናቃኞቹ ጀኔራሎች መካከል በቀጠለው ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ 12 ሚሊዮን የሚሆኑት ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተቋሙ ዘገባ ጠቅሷል፡፡

ወደ ዘጠኝ ሚሊዮን የሚጠጉት በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ መሠረተ ልማቶች በወደሙባቸው አካባቢዎች የሠፈሩ ሲሆን የጅምላ ረሃብ ሥጋትም ተጋርጦባቸዋል።

ዓለም አቀፉ ድርጅት በሱዳን ወደ 26 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ለከባድ ረሃብ መጋለጡን ገልጾ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ሰብአዊ ቀውስ ገጥሟታል ብሏል፡፡

“ከዓለም ሕዝብ ከአንድ ከመቶ ያነሰ የሕዝብ ብዛት ያላት ሱዳን በዓለም የሰብአዊ ርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ተረጅዎች መካከል 10 በመቶውን ትሸፍናለች” ሲል እአአ የአጣዳፊ ርዳታ ፈላጊዎችን የሚከታተለውና መሠረቱን በኒው ዮርክ ያደደረገው ድርጅት እአአ በቀጣዩ 2025 የአጣዳፊ ሁኔታ ክትትል በሚያስፈልጋቸው ቀውሶች ዘገባው አስታውቋል፡፡

ከዓለም ሕዝብ ከአንድ ከመቶ ያነሰ የሕዝብ ብዛት ያላት ሱዳን በዓለም የሰብአዊ ርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ተረጅዎች መካከል 10 በመቶውን ትሸፍናለች”

የዓለም ነፍስ አድን ኮሚቴ ዘገባ በየዓመቱ ለሰብአዊ ቀውስ ተጋላጭነት ከፍተኛ ሥጋት ያለባቸውን 20 ሀገራት ለይቶ በማጉላት የሚያሳይ ሲሆን ሱዳን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በቀዳሚነት ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አመልክቷል፡፡

በሀገሪቱ በጠቅላላው 30.4 ሚሊዮን ሰዎች በሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎች መሆናቸውን የገለጸው ኮሚቴው የተረጅዎችን ቁጥር መመዝገብ ከጀመረ ወዲህ ይህ “ከምንጊዜውም ትልቁ የሰብአዊ ቀውስ” መሆኑን ገልጿል።

ኮሚቴው በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ወደ 305 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የሰብአዊ እርዳታ የሚሹ መሆኑን ዘግቧል፡፡ ከእነዚህ 82 ከመቶ የሚሆኑት በኃይል በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶች፣ ሚያንማር፣ ሦሪያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሊባኖስ በመሳሰሉት ክትትል ያስፈልጋቸዋል ተብለው በተመዘገቡ የቀውስ አካባቢዎች እንደሚገኙ ዘገባው አመልክቷል፡፡

የዓለም ነፍስ አድን ኮሚቴ ኃላፊ ዴቪድ ሚሊባንድ ‘ዓለም እሳት ላይ ነች’ ይህ በመቶ ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የዕለት ተዕለት እውነታ እንደሆነ ግልጽ ነው።” ብለዋል፡፡

ሚሊባንድ አክለውም "ዓለማችን በሁለት ካምፖች እየተከፈለች ነው፤ ባልተረጋጋ እና ግጭት ባለበት ቦታ በተወለዱት እና በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ የመኖር እድል ባላቸው መካከል" ማለታቸውን ኤኤፍፒ ጠቅሷል፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG