በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በዓለም ዙሪያ እየተከበረ ነው


 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም

ዛሬ ዓመታዊው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በዓለም ዙሪያ እየተከበረ ነው።

ከአንድ መቶ በሚበልጡ ዝግጅቶች እየተከበረ ያለው የዘንድሮው የዓለም የፕሬስ ቀን የፕሬስና የዲሞክራሲ ግንኙነትን ዐብይ ርዕሱ አድርጓል።

የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የዚህ የዓለም የፕሬስ ቀን ዋና በዓል አስተናግዳለች።

የ”ለውጥ አራማጁ” የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ሃገራቸው የጥላቻ ንግግር እና የተዛባ መረጃ ስርጭትን ለመታገል የሚያስችል ህግ እያረቀቀች መሆንዋን አመልክተዋል።

ዶ/ር ዐብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን እስከያዙበት እስካለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ድረስ በጋዜጠኛ አሳሪነት የታወቀች እንደነበረች ሲታወስ በእርሳቸው አስተዳደር በርካታ ጋዜጠኞች ከእስር ተፈተዋል ።

ለጋዜጠኞች ደህንነት የሚሟገተው/ሲፒጄ/ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት አንድም የታሰረ ጋዜጠኛ እንደሌለ በተለያዩ መንገዶች የሚወጡ አዳዲስ ህትመቶች እያበቡ መሆናቸውን አመልክቷል። ከአሁን ቀደም ታግደው የነበሩ ከሁለት መቶ ስድሳ በላይ ዌብሳይቶችን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አመራር ወዲህ ተለቀዋል። ወደሃገር እንዳይገቡ ተከልክለው የነበሩ ጋዜጠኞች ለመግባት በቅተዋል።

ያም ሆኖ በሀገሪቱ አሁንም ጋዜጠኞች በተለይ ሁከታማ በሆኑ አካባቢዎች ጥቃት እና እስርን የመሳሰሉ አድራጎቶች የሚጋለጡ መሆኑን /ሲፒጄ/ አስታውቋል።

ትናንት ሃሙስ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ህብረት ባለሥልጣናት የዩኔስኮንና ጊሌርሞ ካኖ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ሽልማትን በእስር ላይ ለሚገኙት የሚያንማር ጋዜጠኞች ኪያው ሶ ኡ እና ዋ ሎን ሰጥተዋል።

ሁለቱ የሮይተርስ ጋዜጠኞች የሚያንማር የጦር ሰራዊት በሮሂንጋ ሙስሊሞች ላይ ስለፈፀመወ ጭካኔ የተመላበት ጥቃት በመዘገባቸው ሰባት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው ታስረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG