በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕ አዲስ ውዝግብ ሲያሥነሱ ባይደን ከፍተኛ የምርጫ ገንዘብ አሰባስበዋል


ትራምፕ አዲስ ውዝግብ ሲያሥነሱ ባይደን ከፍተኛ የምርጫ ገንዘብ አሰባስበዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:10 0:00

ትራምፕ አዲስ ውዝግብ ሲያሥነሱ ባይደን ከፍተኛ የምርጫ ገንዘብ አሰባስበዋል

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ አውጭዎች፣ የሪፐብሊካን ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ ዶናልድ ትረምፕ፣ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ በተከታታይ ለተናገሯቸው አወዛጋቢ አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል።

የዴሞክራቱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ደግሞ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ እና እሑድ በምርጫ ዘመቻ ላይ ባይሆኑም፣ በድጋሚ ለመመረጥ የሚያደርጉት ዝግጅት ዋና መነጋገሪያ ኾኗል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ በዴይተን ኦሃዮ የምርጫ ቅስቀሳቸው ላይ የተናገሯቸው በርካታ አስተያየቶች መነጋገሪያ ሆነዋል። ከእነዚህም አንዱ፣ ቻይና በሜክሲኮ የመኪና ማምረቻ ፋብሪካ እየነገባች መሆኑን ሲተቹ የተናገሩት ይገኝበታል፡፡

ትረምፕ “ድንበር አቋርጦ በሚመጣ እያንዳንዱ መኪና ላይ መቶ በመቶ ታሪፍ እናስቀምጣለን፤ እኔ ብመረጥ እነዚህን መኪኖች መሸጥ አትችሉም፤” ብለዋል፡፡ አያይዘውም “አሁን ካልተመረጥሁ የለየለት ደም መፋሰስ ይሆናል፤ ያም በትንሹ ነው፤ እንዲያውም በመላ አገሪቱ ደም መፋሰስ ይሆናል፤” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኢምግሬሽንና ሥነ ተዋልዶ ለባይደንና ትረምፕ የምረጡኝ ዘመቻ ርእሰ ጉዳዮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:13 0:00

የትረምፕ ምርጫ ዘመቻ ቡድን፣ የትምረፕ አስተያየት “የፖለቲካ ጥቃት እንዳልሆነ” አሥምሮበታል። ሪፐብሊካኑ ሴናተር ቢል ካሲዲ፣ “ሚት ዘፕሬስ” በተሰኘው የኤንቢሲ ቴሌቪዥን ላይ በቀረበቡት ወቅት፣ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን አስተያየት አካፍለዋል።

“የንግግሩ አጠቃላይ ቃና፣ ብዙ አሜሪካውያን፥ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እውን ፕሬዝዳንት መሆን ይገባቸዋልን? ብለው መገረማቸውን የሚቀጥሉበት ምክንያት መሆኑ ነው፤” ብለዋል ቢል ካሲዲ፡፡ አያይዘውም፣ “አንድ ሰው እንደ አመለካከቱ የሚተረጉመው ነው። እርሳቸው ከባይደን ጋራ እየተፎካከሩ ነው፤ ባይደን ደግሞ ‘ፖለቲካዊ ብጥብጥ ነው’ ይላሉ። ደጋፊዎቻቸውም ትራምፕን መከላከል ይፈልጋሉ፤ ስለዚህ የተናገሩት ስለ ኢኮኖሚ አደጋ ነው ይላሉ፤” ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በኤቢሲ “በዚህ ሳምንት” ላይ የቀረቡት የኦሃዮ ሪፐብሊካን ተወካይ ማይክ ተርነር፣ ትረምፕ አንዳንድ ስደተኞችን “ሰዎች አይደሉም” ሲሉ የተናገሩትንና ባይደን በሕገ ወጥ መንገድ ደንበር ስለሚያቋርጡ ስደተኞች ጉዳይ ስላላቸው አያያዝ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ተርነር፣ “በርግጥ ባለፉት ጊዜያት ከሆኑት ጋራ አልስማማም፤ የአሜሪካ ሕዝብም ከእነርሱ ጋራ አይስማማም ብዬ አስባለሁ፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ ግን፣ ሰዎች ዶናልድ ትረምፕ በዚህ ውድድር ውስጥ ይህን ቀውስ ማስተካከል የሚችሉ ብቸኛው ዕጩ መሆናቸውን ያዩታል፤” ሲሉ አመልክተዋል፡፡

በቅዳሜው የምርጫ ቅስቀሳቸው፣ ትረምፕ፥ በዴሞክራቲክ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ላይ የሚሰነዘሩትን ትችት በዕጥፍ ጨምረዋል፡፡ ደጋፊዎቻቸውም በጠቅላላ ምርጫ እንዲሳተፉ አበክረው ጥሪ ሲያቀርቡ አሳሳቢነቱን ችላ በማለት አልነበረም፡፡

በዚህ ምርጫ የእርሳቸው ማሸነፍ አማራጭ የሌለው እንደሆነ የተናገሩት ትረምፕ፣ “ካላሸነፍን በዚህ ሀገር ሌላ ምርጫ የሚኖረን አይመስለኝም። ሌላ ምርጫ የሚኖራችሁ አይመስለኝም ወይም በርግጠኝነት ትርጉም ያለው ምርጫ አይሆንም፤” ሲሉ አሳስበዋል፡፡ “ስለዚህ ለመምረጥ ብንወጣ ይሻለናል፤ በእውነቱ እላችኋለሁ፥ ቀኑን አስታውሱ፤ ኅዳር 5፡፡ በአገራችን ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊው ቀን እንደሚሆን አምናለሁ፤” ሲሉ ለመራጮቻቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የምርጫ ዘመቻቸው በሳምንቱ መጨረሻ ላይ እንዳስታወቀው፣ ፕሬዚዳንት ባይደን በድጋሚ ለሚሳተፉበት የምርጫ ውድድር፣ ከፍተኛው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ መሆኑ የብዙኀን መገናኛን ትኩረት ስቧል። አሁን ባይደን፣ በእጃቸው 155 ሚሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ አለ። ከዚህ ውስጥ 53 ሚሊዮን ዶላር በየካቲት ወር ብቻ የተሰበሰበ ነው፡፡

ይህ ዜና የተሰማው፣ ትላንት እሑድ ረፋድ ላይ፣ ባይደን በዋይት ሐውስ የቅዱስ ፓትሪክን ቀን ለማክበር ለተገኙት በርካታ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ባዘጋጁት ቁርስ ላይ ነበር፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG